Saturday, 07 November 2020 13:52

“ምክር እና ቅኔ” መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  በፀሀፊ አማን ስብሃት የተሰናዳው እና “ምክር ቅኔ” የሚል መጠሪያ  የተሰጠው መፅሀፍ ለንባብ በቃ። መጽሀፉ በዋናነት አስተማሪ የሆኑ ምክሮችና አባባሎች፣ አዝናኝ እና ቁምነገር አዘል ጥቅሶች፣ ስለጤና ወሳኝ ምክሮች፣ለወላጆችና ለተማሪዎች ጠቃሚ የሆኑ ምክሮች፣ የተለያዩ አገራት ምሁራንና ማህበረሰቦች አባባሎችና ሌሎች ጠቃሚ ፅሁፎች እንደተካተቱበት ፀሃፊው በመግቢያው ገልጿል።
በ5 ዋናዋና ክፍሎች ተከፋፍሎ በ115 ገፅ የተቀነበበው መፅሃፍት በ70 ብር ለገበያ መቅረቡንና በጃፋር፣ ሀሁ፣ ሔመንና በሌሎች መፅሀፍት መደብሮች እንደሚገኝ ታውቋል።

Read 10108 times