Saturday, 14 November 2020 10:10

አዲስ አበባን ጨምሮ ሽብር ጥቃት ሊፈፅሙ ያቀዱ 150 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

  የህወሃት ተልዕኮን ተቀብለው በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ሲንቀሳቀሱና ሁከት ለማነሳሳት ሞክረዋል የተባሉ 150 ህል ሰዎች  መታሰራቸውን መንግስት አስታወቀ።
የጠ/ሚንስትሩ ጽ/ቤት ለመገናኛ ብዙሃን ባሰራጨው መግለጫው ህውሃት ያሰማራቸው ቡድኖች በአዲስ አበባ እና በሌሎች  የሃገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለማድረስ የሽብር አስፈጻሚ መረብ ማቋቋማቸውን ነው ያስገነዘበው።
በዚህም በወንጀል ድርጊት ተሳትፎ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በአዲስ አበባ እና በተለያዩ አካባቢዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን መግለጫው ያስገነዝቧል።
በወንጀል ተጠርጥረው እየታሰሩ ያሉትም ከአንድ ብሄር ሳይሆን ከተለያዩ ብሄር አባላት መሆናቸውን ቁጥራቸውም እንደሚጋነነው ሳይሆን 150 መሆናቸው የተመለከተ ሲሆን  ፖሊስ አፋጣኝ ምርመራ እያደረገ በዋስ መፈታት ለባቸውን እየፈታ መሆኑም ተመልክቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳመለከተው በተከናወኑ ፍተሸዎች 18 ያህል ቦንቦች፣ ከ7 መቶ በላይ ሽጉጦች፣ ከ4 ሺ በላይ ጥይቶች፣ የመገናኛ ሬዲዮኖች፣ የጦር ሜዳ መነጽሮች እና የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎች መገኘታቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅት አለማቀፍ ተቋማትና ግለሰቦች ያልተጣራ መረጃ እያመነጨ መሆኑን ያመለከተው የጠ/ሚንስቴር ጽ/ቤት ግለሰቦችና ተቋማት ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

Read 11948 times