የአፍሪካ ህብረት የፀጥታ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ገ/እግዚአብሔር መብራቱ ከኃላፊነታቸው የተነሱ ሲሆ ከፀረ ኃላፊነታቸው የተነሱት የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር፤ የታማኝነት ችግር አለባቸው የሚል የቅሬታ ደብዳቤ ለህብረት በማቅረቡ ነው ተብሏል።
ሮይተርስ በዘገባው የፀጥታ ኃላፊው በኢትዮጵያ የፌደራል መንግስትና በህውሃት መካከል እየተደረገ ባለው ጦርነት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለመወጣት ቁርጠኛ አለመሆናቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር በቅሬታ ደብዳቤው ላይ ገልጿል።
በዚሁ መሰረትም የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ሙሳፋቂ ማህማት፣ የፀጥታ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ገ/እግዚአብሔር መብራቱን ከኃላፊነታቸው አንዲነሱ ማድረጋቸውን ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።