Saturday, 14 November 2020 10:43

የሰምና ወርቅ 3ኛው ዓመታዊ የመፅሀፍት አውደ ርዕይ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


            በሰላምና ወርቅ ኢንተርቴይመንትና ኢቨንት በየአመቱ የሚካሄደው 3ኛው ዙር የመፅሀፍት አውደ ርዕይ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይከፈታል። ይህ አውደ ርዕይ ከኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ ተቀዛቅዞና ተጎድቶ የነበረውን የንባብ ባህል ከማነቃቃቱም በላይ ለመፅሐፍት ገዢዎች ከ20-50 በመቶ ቅናሽ የተደረገባቸውን መፅሀፍ ማግኘት የሚቻልበትን እድል ያመቻቻል ተብሏል።
እስከ ህዳር 21 ቀን በሚቆየው በዚህ አውደ ርዕይ በርካታ የመፅሀፍት መደብሮች ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በ10 ቀናት ኮንበብ ጋር የተያያዙ ሌሎች መርሃ ግብሮች ጎን ለጎን እንደሚከናወኑ የአውደ ርዕዩ አዘጋጅና የሰምና ወርቅ ኢንተርቴይመንትና ኢቨንት መስራችና ባለቤት ጋዜጠኛ ጌታቸው ዓለሙ አስታውቋል።

Read 3336 times