Saturday, 21 November 2020 09:58

የሮኬት ጥቃቱ አማራ መገናኛ ብዙኃንን ዒላማ ያደረገ ነበር ተባለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)

  ህወሃት ለሁለተኛ ጊዜ ትናንት ከሌሊቱ 2፡30 ላይ ወደ ባህር ዳር ያስወነጨፈው የሮኬት  ጥቃት ኢላማ የአማራ መገናኛ ብዙሃን የባህር ዳር አየር ማረፊያና የቴሌኮም ታወሮች እንደነበሩ  የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀው።
ህወሃት ወደ ባህር ዳር ለሁለተኛ ጊዜ ያስወነጨፈቻቸው ሮኬቶች ሁለት ሲሆኑ አንደኛው የበቆሎ እርሻ ላይ ሲያርፍ፣ ሌላኛው ሜዳ ላይ በማረፍ የታለመላቸውን ኢላማ ሳይመቱ መክሸፋቸው ተጠቁሟል።
 ባለፈው ሃሙስ ሌሊት በህወሃት የተወነጨፈው ሮኬት ንፁሃንን ዒላማ ያደረገ ነው ያለው የክልል መንግስቱ፤ይህም የሽብር ተግባር ፤የህወሃትን የሽብር ዒላማዎች የማክሸፉ ተግባር በቀጣይም ያለመዘነጋት ይሰራል ብሏል።
የህወሃት ቡድን ከሳምንት በፊት ነበር የመጀመሪያዎቹን ሁለት ሮኬቶች ወደ ባህር ዳርና ጎንደር ያስወነጨፈው፤ምንም እንኳን ጉዳት ሳያደርሱ መክሸፋቸው ቢገለፅም።
የህወሃት ቡድንኑ በሀገር ውሰጥ ጥቃት  ብቻ አልተወሰነም፡፡ በኤርትራ ፣አስመራም  የሮኬት ጥቃት  የፈጸመ ሲሆን ያለ ምንም  ጉዳት መክሸፉ ተጠቁ    ሟል፡፡ ይህን የህወሃት የሮኬት ጥቃት የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት “ቀጠናውን ወደ ለየለት ትርምስ ለመክተት ያለመ ሙከራ ነው” ሲል ድርጊቱን ማውገዙ ይታወቃል። ህወሃት በንጹሃን ላይ ጉዳት ከሚያደርስና አካባቢውን ወደ ትርምስ ሊያስገባን መሆንንነ ገልጿል ከሚችል ድርጊት እንዲቆጠብ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳስቧል።
ከዚሁ   የህግ ማስከበር ጦርነት ጋር በተያያዘ፣ ግጭቱ በፍጥነት ያበቃ ዘንድ  ሁለቱም ወገኖች እንዲሰሩ የአሜሪካን መንግስት  አሳስቧል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ፀሃፊ ቲቦር ናጅ  ባለፈው ሃሙስ  በጉዳዩ ላይ ለጋዜጠኞች በኦንላይን በሰጡት መግለጫ፤ ህወሃት በጎንደር ፣ ባህርዳርና አስመራ  የፈፀመው  የሮኬት ጥቃቶች ተቀባይነት የሌለው፤ ሁኔታውን የበለጠ የሚያወሳስብና  ክፉ አላማን ያነገበ ነው በማለት አወግዘውታል።
ግጭቱ በሚያበቃበት ሁኔታ ላይም በአሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎችን ጨምሮ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ቲቦር ናጅ አስታውቀዋል።
የማይካድራው ጥቃት በህወሃት መፈጸሙን ያወሱት ቲቦር ናጅ፤ “ጥቃቱ በእጅጉ የሚወገዝ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ጥሰት” ነው። የህወሃት ቡድን  በተለይ የኤርትራን መንግሰት ወደ ጦርነቱ ስቦ በማስገባት ጦርነቱም ለማራዘምና ለማስፋት በማለም ወደ አስመራ  የሮኬት ጥቃት ቢፈጽሙም ያሰበው  ካልሆነም ይልቁን ዓለማቀፍ ውግዘትን  አስከትሎባቸዋል።


Read 9876 times