Saturday, 21 November 2020 10:38

ከፌስቡክ ገጾች በጨረፍታ

Written by  አንሙት አብርሃም
Rate this item
(0 votes)

 የ47 ዓመታት ፖለቲካ ፍፃሜ ወዴት
                  

            ህወሓት በዛሬ አቋሙ፣ በኢትዮጵያ ህዝብን አቆራርጦ የመለያየት አጥፍቶ የመጥፋት አማራጭ እየተገበረ መስሎኛል።
ልብ ብለህ አጢናቸው!
በመላ አገሪቱ ባሉ የመከላከያና የፀጥታ ተቋማት ከትግራይ የወጣ አባልና አመራር በሌሎች ጓዶቹ ላይ ግድያና እገታ እንዲፈፅም ጊዜ ወስዶ ሲመለምልና ሲያስፈፅም ፥ ምናልባት ከዚህ በኋላ በአገሪቱ የፀጥታ ተቋም ውስጥ የትግራይ ተወላጅ አባልና አመራር ሆኖ እንዳይቀጥልም ጠባሳ የማስቀመጥ ነው። ይሔ አገር የማፍረስ እርምጃ ነው!
የትግራይ ህዝብን ዘር ማጥፋት ታውጆብሃል፣ ሊያጠፉህ እየመጡ ነው ብለውታል፥ እያሉት ነው!
ይህን ለማስረገጥ ሑመራ ላይ የሠራውን እንመልከት!
በእኔ እምነት ህዝቡ ከሑመራ ወደ ሱዳን እንዲሰደድ ያደረገው ህወሓት ነው!
አንድም “ዘር ማጥፋት ታውጆብሃል፣ ሊያጠፏችሁ ነው” የሚለውን ለማስረገጥ “ከጥፋት ራሳችሁን አድኑ” ለማለት እንዲወጡ አድርጓል፤
ጉዳዩ መጠፋፋት መሆኑን ለማሳየት ደግሞ በታጣቂዎቹ ድጋፍ የቀን ሠራተኞች የሆኑ አማራዎችና ሌሎች እንዲጨፈጨፉ አስደርጓል፤
የቀረውን ህዝብ ራስህን አድን በሚመስል መልኩ እንዲወጣ መስራቱን እረዳለሁ።
ይሄ ለህዝቡ ከሰበከው “የዘር መጠፋፋት” ስዕል በተጨማሪ በስደተኞቹ ሰበብ ወታደራዊ እርምጃው አለማቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ ተጠቀመበት።
ከሑመራ እስር ቤት ታግተው የተወሰዱትንና የተገደሉትን አማራዎች ይዘህ ወደ ራያ እንሒድ
ራያ ላይ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ወደ ሌላ አገር እንዲሰደዱ ለማድረግ አይመችም ፤ ስለዚህ እየመረጠ ወደ መሐል ትግራይ ማጓጓዙን ሰምተናል።
የአንዳንዶች ስጋት ራያን ለመጨፍጨፍ አስቦ ነው ቢሉም፣ እኔ የገባኝ “የሚመጡት ዘርህን ሊያጠፉት ነው” የሚለውን ፕሮፓጋንዳ ለማስረገጥና ህዝቡ እንዲያምን ለማድረግ ነው።
እንደ ሑመራው የቀረውን አማራ የመጨፍጨፍ እርምጃ ባይወስድም፣ እንደ ሑመራው መያዣ ተደርገው የታገቱ እስረኞች፣ ነጋዴዎች፣ የመንግስት ሠራተኞች አሉ።
ከአንድ ሺህ በላይ እንደሚሆኑ የተነገረ ቢሆንም፣ የትግራይ ተወላጆችን ጨምሮ ከአስር ሺህ በላይ የሚሆኑ ራያን ለቀው እንዲወጡ በውድም በግድም ሠርቷል።
ህዝቡን ከራያ መውሰድ አንድም በመሐል ትግራይ ላለው ህዝብ “የተፈናቀሉ ናቸው” ለማለት እና ህዝቡ ዞሮ ጦርነቱን እንዲቀላቀል ሊሆን ይችላል።
ህወሓት ጦርነቱን ለደጀን ቀረብ አድርጎ ለመዋጋትም ስለተገደደ።
ህዝብን መለያየትና አገር የመበተን ስብከት ለተዋጊው ህወሓት ያሰለፋቸውን ለጋ ወጣቶች : “ኢትዮጵያ አገራችሁ አይደለችም ፥ ልታጠፋችሁ ጦርነት ከፍታለች” እያለ ጦር ሜዳ ይልካቸዋል።
“እጃችሁን ከሰጣችሁ ይረሽኗችኋል” ብሏቸው ታዳጊዎቹ ቆስለው ለሕክምና ሲሄዱም ያለቅሱ ነበር። ልንረሸን ነው ብለው!
“ቆስላችሁ ወይም ተማርካችሁ ከያዟችሁ በመርዝ ይገድላችኋል” ብሏቸው የትግራይ ልዩ ኃይል ታካሚዎች ምግብና ውሃ ለመውሰድ ሐኪሞች እየቀመሱ ይሰጧቸዋል።
“አማራ ጭራቅ ነው፥ ጠላታችሁ ነው ሊያጠፋችሁ ወሯችኋል” ብሏቸው ኖሮ፣ እጃቸውን የሰጡት የተነገረንና የጠበቀን አይገናኝም እያሉ ናቸው።
ይሔ በትግራይና በሌላው ኢትዮጵያዊ መካከል የማይጠገን ሰባራ በመፍጠር፣ እነሱ ቢጠፉም የቀረው የትግራይ ህዝብ ታግሎ ነፃ ትግራይን ያውጃል የሚል ይመስለኛል።
የ47 ዓመት ፖለቲካ ፍፃሜ እንዲህ እንዲሆን ተመረጠ መሰለኝ?
እስከ ዛሬ አየናችሁ፤ ከእንግዲህ በቃችሁ፤ እኛ እንሞክረው የሚል እንኳ እንዳይኖር መደረጉ አሳዛኝ ፍፃሜ ነው።

Read 2695 times