Saturday, 28 November 2020 00:00

አለማቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር የህወኃትን ሃሰተኛ መረጃ አጋላጠ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

 ከሰሞኑ ህወኃት "858 የተማረኩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን ለአለማቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር አስረክቢያለሁ" ቢልም፤ ማህበሩ የህወኃት መግለጫ ሃሰተኛ ነው ብሏል፡፡
አለማቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር፣ በአሁኑ ወቅት በጦርነት ሰብአዊ ጉዳት ለሚደርስባቸው ድጋፍ ለማድረግ ከመሞከር ያለፈ ተግባር እያከናወነ አለመሆኑን ገልጾ፤ "858 የመከላከያ ሰራዊት አባላትንም ከህወኃት አልተቀበልኩም" ብሏል፡፡
ማህበሩ የሰብአዊ ተግባሩን ገለልተኛ ሆኖ የሚያከናውን እንደመሆኑ ሁለቱን ሃይሎች የማግባበት ሆነ የማደራደር ሚና እንደሌለው ነው በመግለጫው ያመለከተው፡፡
የታስሩ ሰዎች አስለቅቀን የሚል ጥያቄም ከመንግስት እንዳልቀረበለትና ምንም አይነት እስረኞችን የማስፈታት ጥረት እያደረገ አለመሆኑንም ነው ማህበሩ ያስረዳው፡፡ እስረኞች የማስፈታትና የማመላለስ ተግባር እንዲያከናውን ከመንግሰት ጥያቄ ከቀረበለት ግን ይህን ሰብአዊ ተግባሩን ያለ ማወላዳት እንደሚወጣም አለማቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር በመግለጫው አትቷል፡፡  


Read 1439 times