Print this page
Sunday, 29 November 2020 15:44

“ማህደረ ደራሲያን” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የደራሲያኑን ሜሪ ጃፋር፣ ሲሳይ ንጉሱ፣ ረ/ፕ ደረጀ ገብሬ፣ ይታገሱ ጌትነት፣ አስፋው ዳምጤ፣ አበረ አዳሙ፣ አፈወርቅ በቀለ፣ እነዬ ሽበሺ፣ ደበበ ሰይፉ፣ ታደለ ገድሌ (ዶ/ር)፣ ገስጥ ተጫኔ፣ ፀሀይ መላኩና ፀሀፊ ተውኔናትና ገጣሚ አያልነህ ሙላቱን ጨምሮ የ35 እውቅ ደራሲያንን የህይወት ታሪክ የያዘው “ማህደረ ደራሲያን” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ።
መጽሐፉ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በነፃ የታተመ ሲሆን ማተሚያ ድርጅቱ 7 ሺህ ቅጂ ለደራሲያን ማህበር ማክሰኞ ጥር 15 ቀን 2013 ዓ.ም አስረክቧል። በ359 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ55 ብር ለገበያ ቀርቧል። በርክክቡ ስነ-ስርዓት ላይ የደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት ደራሲና ባለቅኔ አበረ አዳሙ፣ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ዋና ስራ አስኪጅ አቶ ሽታሁን ዋለ እና ታሪካቸው በመፅሀፉ የተካተተላቸው ደራሲያን ተገኝተው ለማተሚያ ድርጅቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Read 10203 times