Tuesday, 08 December 2020 13:48

የግጥም ጥግ

Written by  ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
Rate this item
(5 votes)

 ዘራፍ ቀርቶ ቀረርቶ
ትዕግስት ተተክቶ
ጡንቻን በእርጋታ
ማስተዋል ሲረታ
ለሚል አልሻገር
የማይገባው ፍቅር
እራሱን ሲቀብር
እምዬን ለማላቅ
እርሱ የሚሳቀቅ
ሕዝብን የሚያስቀድም
ስራው የሚያስደምም
አላልፍ ያለው ያልፋል
ቋጠሮ ይፈታል
ምርጫም ይደረጋል
ያላመነው ያምናል
የማታ የማታ
ድንቅ ነሽ በፌሽታ
ሆኖላት እፎይታ
ይቀራል ስሞታ
(ሰማንህ አየንህ)
ፈጣሪን ስትጠራ
ወጣ ከአንተ ጋራ
(እንግዲህ)
ማረንና ምራን
ከትከሻህ ወረድን

Read 2581 times