Saturday, 12 December 2020 00:00

ኦነግ ሸኔ እና ህወኃት በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ባልደራስ ጠየቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 ከምርጫው በፊት ህገ መንግስቱ ላይ ህዝበ ውሳኔ ይካሄድ”
                           
              “ህወኃት” እና “ኦነግ ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የጠየቀው “ባልደራስ” ፓርቲ፤ ባለፉት ዓመታት ከሰሜን ጎንደርና ወሎ የተወሰዱ የአማራ መሬቶች እንዲመለሱ ብሏል፡፡
ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በህወኃት፤ ላይ መንግስት የወሰደውን እርምጃ እንደሚደግፍ ጠቁሞ ከዚህ ቀደም ጥያቄ ሲቀርብባቸው የቆዩና በህወኃት በጉልበት የተወሰዱ የሰሜን ጎንደር አካል የነበሩት ወልቃይት፣ጠገዴና ሁመራ እንዲሁም የሰሜን ወሎ አካል የነበረው ራያ ወደ አማራ ክልል እንዲከልሉ ጠይቋል፡፡
ህወኃት በስልጣን በቆዩበት ወቅት በርካታ ኢ-ሰብአዊ ተግባራትን መፈፀሙን፣ ኤርትራን ማስገንጠሉን እንዲሁም በሃገሪቱ መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈፀሙንና ማስፈፀሙን የጠቀሰው ባልደራስ፤ ፓርቲው በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ጠይቋል፡፡
በተመሳሳይ በተለይ ባለፉት 2 ዓመታት ኦነግ ሸኔ ዘርና ማንነት መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋ መፈፀሙን በማስረዳት፣ በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ  ባልደራስ ጠይቋል፡፡ በአስር ላይ የሚገኙ አመራሮቹ እንዲፈቱ የጠየቀው ባልደራስ ቀጣይ ምርጫ ከመካሄዱ በፊትም በህገ መንግስቱ ላይ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የጠየቁ ሲሆን በእስር ላይ የሚገኙ አመራሮቹም እንዲፈቱለት አሳስቧል።
በቅርቡ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ህወሃትና ኦነግ ሸኔ በአሸባሪነት መፈረጅ እንዳለባቸው መሞገታቸው አይዘነጋም።


Read 8118 times