Saturday, 12 December 2020 00:00

ኢትዮጵያ ወደ ነበረችበት የከፍታ ዘመን” የጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ዩቶጵያ ትሬዲንግ የተሰኘ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ድርጅት ያሰናዳው “ዘመን” የሚል መጠሪያ ያለው የኪነ ጥበብ ዝግጅት የፊታችን ሰኞ ታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም በአምባሳደር ቲያትር አዳራሽ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ ይካሄዳል። በዕለቱም የባህልና የጃዝ ሙዚቃ ኢትዮጵያንና አባይን ትኩረት አድርገው የተገጠሙ የተመረጡ ግጥሞች፤ስለ አባይና ታላቁ የህዳሴ ግድብ መነባነብ ሃሳብ ለታዳሚዎች የሚቀርብ ሲሆን፣ ይህ ዝግጅት በ16 ፊልም ፕሮዳክሽን በአግባቡ ተቀርፆ በሬዲዮና በቴሌቪዝን ለአደማጭና ተመልካች ይቀርባል ተብሏል፡፡
በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የሚመሰገኑ እና የሚሸለሙ እንዳሉ የተጠቆመ ሲሆን “ዘመን በዩቶጵያ” በሚል  የተሳታፊዎችን ህይወት ልምድና ገጠመኝ ያካተተ አነስተኛ ጋዜጣ ታትሞ ለታዳሚያን እንደሚቀርብ የመርሀ ግብሩ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዘሪሁን ታዬ(የበየነች) ገልጿል፡፡

Read 892 times