Saturday, 12 December 2020 00:00

የጋዜጠኛ ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን “ነፃነት” መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የአንጋፋው ጋዜጠኛና ገጣሚ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን የግጥምና የወግ ስብስብ የሆነው “ነፃነት” መፅሐፍ ዛሬ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአራዳ ጊዮርጊስ ከፍ ብሎ በሚገኘው ሶርአምባ ሆቴል በድምቀት ይመረቃል።
በኢትዮጵያ ታሪክ በህዝብ ትብብር (በደቦ) የታተመው ይሄው መፅሐፍ በስነ-ፅሁፍ ተመራማሪው ይታገሱ ጌትነት እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአለ ስነ-ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ዳይሬክተርና መምህር አገኘሁ አዳነ ድልነሳሁ የዳሰሳ ፅሁፍ ይቀርብበታል የተባለ ሲሆን፣ በዕለቱም አርቲስትና ጋዜጠኛ ተፈሪ ዓለሙ ጋዜጠኛ ዘካሪያ መሃመድ፣ ገጣሚያኑ ምስራቅ ተረፈ፣ ምልዕቲ ኪሮስ፣ ጋዜጠኛ ዙበይዳ አወል፣ ማህደር አካሉ፣ ስመኝ ግዛውና ሌሎችም ግጥሞችና መነባንቦችን እንደሚቀርቡ፣ መድረኩን ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ እንደሚመራውም ታውቋል።

Read 8185 times Last modified on Monday, 14 December 2020 19:41