Print this page
Saturday, 12 December 2020 00:00

“አናርያን ፍለጋ” አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


          በምህንድስና ባለሙያው ወንድም ስሻ አየለ አንገሎ የተሰናዳውና ከሸካ እስከ “ኩሽ” ድረስ ታሪክንም፣ ባህልን፣ የአካባቢወን ስነ-ልቦናና ወግ የሚመረምረው “አናርያን ፍለጋ” አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ።
መፅሐፉ የሸካን ሁለንተናዊ ህይወት፣ ከትናንት እስካሁን ያለውን እውነታ የምርምር ውጤቶችን መነሻ በማድረግ ዳጎስ ባለ እትም ለንባብ ያበቃ ሲሆን መጽሐፉ በአንካቢው ወደፊት ምርምር ለሚያደርጉ ምሁራን ጥሩ ግብአት ይሆናል ብሎ እንደሚያን ደራሲው በመግቢያው ገልጿል። መፅሐፉ በሸካ ሞቻ ታሪክ ውስጥ ስላሉ አከራካሪ ነጥቦች፣ ስለ ሸካ መንግስት አወቃቀርና ሀተታው፣ ስለሌሎች ነገዶች ታሪኮች ቅኝትና ስለ ሸከካ አናርያ ተዛማጅ ጭብጦች፣ ስለ ኩሽ ጥንት ከሸካ አንፃር በሚሉና በመሰል ጉዳዮች በዋናነት ትኩረቱን አድርጓል። በሁለት ዋና ዋና ክፍሎችና በሰባት ምዕራፎች ተከፋፍሎ የተሰናዳው መፅሐፉ በ388 ገፅ ተመጥኖ በ300 ብርና በ25 ዶላር ለገበያ ቀርቧል።

Read 8418 times Last modified on Monday, 14 December 2020 19:42