ባለፈው የፈረንጆች አመት 2019 አለማቀፍ የጦር መሳሪያ ሽያጭ የአሜሪካ ኩባንያዎች ቀዳሚነትን መያዛቸውንና አገሪቱ በአመቱ በመላው አለም ከተከናወነው የጦር መሳሪያዎች ሽያጭ 61 በመቶ ያህሉን መያዟን ስቶክሆልም ኢንተርናሽናል ፒስ ሪሰርች ኢንስቲቲዩት የተባለ አለማቀፍ ተቋም ከሰሞኑ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡
ከአለማችን የአመቱ ባለከፍተኛ ገቢ 25 ታላላቅ የጦር መሳሪያ አምራችና ሻጭ ኩባንያዎች ያገኘውን መረጃ መሰረት አድርጎ ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት እንዳለው፣ ኩባንያዎቹ በአመቱ በድምሩ ከጦር መሳሪያዎች ሽያጭ 361 ቢሊዮን ዶላር አግኝተዋል፡፡
ከ25ቱ ኩባንያዎች መካከል ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ያለውን ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገቡት የአሜሪካዎቹ ኩባንያዎች ሎክሄድ ማርቲን፣ ቦይንግ፣ ኖርዝሮፕ ግሩማን፣ ሬቲዮንና ጄኔራል ዳናሚክስ ሲሆኑ፣ ኩባንያዎቹ በአመቱ 166 ቢሊዮን ዶላር ከጦር መሳሪያ ሽያጭ ማግኘታቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡ የጦር መሳሪያዎች ሽያጭ በ2018 ከነበረበት የ8.5 በመቶ እድገት ማሳየቱን የጠቆመው ዘገባው፣ በአመቱ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ካስመዘገቡት 25 ኩባንያዎች መካከል የተካተቱት 4 የቻይና ኩባንያዎች በሽያጭ ሁለተኛ ደረጃን ወይም 16 በመቶ ድርሻን ይዘዋል፡፡
ከ25ቱ የአለማችን ታላላቅ የጦር መሳሪያ ኩባንያዎች ተርታ ለመሰለፍ የበቃው የመጀመሪያው የመካከለኛው ምስራቅ አገር ኩባንያ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትሱ ኢጅ ሲሆን፣ ከአመቱ ሽያጭ የ1.3 በመቶ ድርሻ በመያዝ በ22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ከኩባንያዎቹ መካከል በአመቱ ከፍተኛ አመታዊ ሽያጭ ያስመዘገበው ኩባንያ የፈረንሳዩ ዳሶልት አቪየሽን ግሩፕ ሲሆን፣ ኩባንያው በ2018 ካስመዘገበው ሽያጭ የ105 በመቶ ጭማሪ ማስመዝገቡ ተነግሯል።
Published in
ከአለም ዙሪያ
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል