Saturday, 19 December 2020 09:58

ፓሪስ “ለሴቶች አድልተሻል” ተብላ የገንዘብ ቅጣት ተጣለባት

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  የፈረንሳዩዋ ርዕሰ መዲና ፓሪስ ከሚገባው በላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሴቶችን ወደ ስራ ገበታ በማሰማራት “ለሴቶች አድልተሻል፤ ወንዶችን በድለሻል” ተብላ የ110 ሺህ ዶላር የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባት አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ከሰሞኑ ባወጣው ዘገባ አስነብቧል፡፡
የፈረንሳይ መንግስት የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር፣ ፓሪስ የጾታ እኩልነትን በሚያዛባ መልኩ በርካታ ሴቶችን በተለያዩ የሙያ መስኮች በመቅጠር ህግ ጥሳለች በማለት በከተማዋ ላይ የገንዘብ ቅጣት መጣሉን የጠቆመው ዘገባው፤ ውሳኔውን የተቃወሙት የፓሪስ ከተማ ከንቲባ አና ሂዳልጎ ግን፣ “ቅጣቱ እጅግ አደገኛ፣ ኢ-ፍትሃዊ፣ ሃላፊነት የጎደለውና ለማመን የሚያዳግት ነው” ማለታቸውን አመልክቷል፡፡
በፈረንጆች አመት 2018 በፓሪስ ከተማ ምክር ቤት ውስጥ ከተቀጠሩት የአስተዳደር ሰራተኞች መካከል 69 በመቶው ሴቶች እንደነበሩ ያስታወሰው ዘገባው፣ ይህም በህግ ከተቀመጠው ውጭ በመሆኑ ሚኒስቴሩ በከተማዋ ላይ ቅጣት እንዲጥል እንዳነሳሳው አክሎ ገልጧል፡፡

Read 2867 times