Print this page
Saturday, 19 December 2020 11:51

“ኑ አገር እናሻግር” የኪነ-ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(4 votes)

በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን የተዘጋጀውና በየወሩ የሚካሄደው የኪነ-ጥበብ ምሽት በዚህ ወር መሰናዶ “ኑ አገር እናሻግር” በሚል ርዕስ የፊታችን ሰኞ ታህሳስ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሄራዊ ቴአትር ይካሄዳል።
በእለቱ ወግ፣ ዲስኩር፣ ግጥምና ሙዚቃ ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን፣ ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር)፣ መምህር አገኘሁ አዳነ፣ ወዳጄነህ ማህረነ (ዶ/ር) አበባው አያሌው (ረ/ፕ) ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ገጣሚ ገዛኸኝ ፀጋው (ዶ/ር)፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ ዮናስ አብርሃም፣ ገጣሚ በላይ በቀለ ወያና መምህርነት ዕፀገነት ከበደ ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን “ሻሎም ኢትዮጵያ” የሙዚቃ ቡድን ዝግጅቱን ያደምቃል ተብሏል። የመግቢያ ዋጋው 200 ብር ሲሆን የመግቢያ ትኬቶቹ ጃፋር ፣ አይናለም፣ ዮናስ መጽሀፍት መደብሮች፣ በጣይቱ ሆቴልና ካዛንቺስ በሚገኘው ጆሲ ልብስ ስፌት ቤት በመሸጥ ላይ ናቸው ተብሏል።

Read 21798 times