Saturday, 26 December 2020 09:44

ቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ግንቦት 28 ይካሄዳል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

 ከ20 በላይ ፓርቲዎች ቢሰረዙም፣ ቁጥራቸው እየጨመረ ነው

          ቀጣዩ ብሄራዊ ምርጫ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ ትናንት ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ባደረገው ምክክር ተወስኗል። የምርጫው የመጨረሻ ውጤትም ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ይፋእንዲደረግ የእጩዎች ምግዘባ ይካሄዳል። ከየካቲት 8 እስከ ግንቦት 23 ደግሞ የምረጡኝ
ቅስቀሳ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል። የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 21 የሚደረግ ሲሆን ግንቦት 28 በሀገር አቀፍ ደረጃ የድምፅ መስጫ ቀን ይሆናል ተብሏል። በዚሁ እለት የክልልነት ጥያቄ ያነሱ የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች የክልልነት ጥያቄ ላይም የህዝቡ ውሳኔ ድምጽ እንደሚሰጥ
የቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ አመልክቷል። በሌላ በኩል፤ የአዲስ አበባ ከተማና በጊዜ ሰሌዳው የተመለከተ ሲሆን ከየካቲት 8 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም የድሬድዋ አስተዳደር ምርጫ ደግሞ ሰኔ 5 ቀን 2013 ይካሄዳል ተብሏል። በሌላ በኩል የምርጫ ቦርድን የምዝገባ መስፈርቶች ያላሟሉ ከ20 በላይ ፓርቲዎች ቢሰረዙም አሁንም ቁጥራቸው እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አለመሆኑን ቦርዱ አስታውቋል::

Read 11419 times