Saturday, 26 December 2020 09:48

ኦነግ በሃገር ውስጥ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ ያካሂዳል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

  መሰረት የአመራር ውዝግብ ውስጥ የገባው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው አቅጣጫ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ ችግሩን ለመፍታት እንቅስቃሴ መጀመሩን አመራር የድርጅቱ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለአዲስ አድማስ አስታወቁ። “የምርጫ ቦርድ ያስቀመጠው የችግር መፍቻ አማራጭ፣ እኛ የምንፈልገውና ያመላከትነው ነው” ያሉት በአቶ ቢቂላ አራርሶ የሚመራው የኦነግ ቡድን አመራር አባላትና ቃል አቀባይ አቶ ቀጄላ መርዳሳ፤ ፓርቲው ከተመሰረተ በኋላ የመጀመሪያና ታሪካዊ የሆነውን ጠቅላላ ጉባኤ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ያካሂዳል ብለዋል።
ኦነግ በሀገር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ እንደማያውቅና የጠቅላላ ጉባኤ ዝግጅት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሂደቱ ቀደም ብሎ ካለፈው አመት መጋቢት ወር ተጀምሮ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ቀጄላ፤ ይሁን እንጂ በፓርቲው ውስጥ በተፈጠሩና በሃገሪቱ በተከማቹ የፖለቲካ ችግሮች ሳቢያ የአዘጋጅ ኮሚቴው አባላት በአሁኑ ወቅት ግማሹ በእስር ላይ ግማሹም ከሃገር በመውጣታቸው አዲስ አዘጋጅ ኮሚቴ ለማቋቋም የሰሞኑን ምርጫ ቦርድ ባለበት ሁለቱ የኦነግ አካላት ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል። እስከ 6 መቶ የሚደርሱ አባላት ይታደሙበታል በተባለው የኦነግ ጠቅላላ
ጉባኤም የ ፓርቲው የ ፖለቲካ ፕ ሮግራም ይፈተሻል፣ ህገ-ደንቡ ይሻሻላል፣ አዳዲስ አመራሮችም ይመረጣሉ ተብሏል። ታስረዋል የተባሉ የኦነግ አመራር
አባላትንም በተመለከተ “የኛ ልዩነት ያለን ከሊቀ መንበሩ ጋር እንጂ ከሌሎች አባላት ጋር አይደለም” ያሉት አቶ ቀጄላ “የእገሌ አባል ተብሎ የሚለይ የለም፤ ኦነግ ነኝ ያለ ሁሉ የኦነግ አባል ነው። የታሰሩ አባላትም ጉዳያቸው በአፋጣኝ ታይቶ ሊፈቱ ይገባል፤ እኛም ትግል እናደርግበታለን” ብለዋል።
በታሰሩ አባላት ጉዳይ ከመንግስት ጋር የከረረ መካሰስ ውስጥ ሳንገባ እንዲፈቱ ጥያቄ ስናቀርብ ቆይተናል፡፡ በዚህም ጥያቄ ስናቀርብ ቆ ይተናል፡፡ በ ዚህም ጥ ያቄም የተፈቱም በርካቶች ናቸው፡፡። በቀጣይም ጥያቄያችንን ማቅረብ እንቀጥላለን ብለዋል አቶ ቀጄላ። ሃገራዊ ፓርቲ መሆኑ በምርጫ ቦርድ
የተረጋገጠው ኦነግ፤ በቀጣይ ፅንፍ የወጣ የተካረረ የፖለቲካ አካሄድን በምንም መልኩ አይከተልም፤ በዚህ መስመር የሚካሄዱትንም ይቃወማል ያሉት አቶ
ቀጄላ፤ እንደ ሀገራዊ ፓርቲነቱ ሃገራዊ ሃላፊነቶችን መወጣት የሚያስችለውን አካሄድ ይከተላል ብለዋል።

Read 12135 times