Saturday, 26 December 2020 17:23

“አረረም መረረም ማህበሬን ተወጣሁ”

Written by 
Rate this item
(4 votes)

 ከእለታት አንድ ቀን አንድ የንጉስ አጫዋች፣ ንጉሱንና ንግስቲቱን
እያጫወተ ሳለ፣ መልአከ ሞት መጥቶ ትኩር ብሎ ተመልክቶት አለፈ።
ድንክዬው የንጉስ አጫዋች በጣም ተጨነቀ።
ንጉስና ንግስቲቱ ባረፉበት አልጋቸው ላይ መኝታ ቤታቸውን ለሄዶ
አንኳኳ።
“ማነው” አለች ንግስቲቱ
“እኔ የንጉስ አጫዋቹ ድንክዬ ነኝ”
“ምን ቸግሮህ ነው” ግባና አስረዳን ? ? ?
“ንጉስ ሆይ፤ በሰላም እርስዎን እያጫወትኩ በነበርኩበት ሰዓት፤ መልአከ
ሞት መጥቶ ትኩር ብሎ አየኝ፡፡ ምን አጠፋሁ አማልዱኝ ንጉስ ሆይ?”
“ግዴለም ለጊዜው ወደ ህንድ ሀገር እንልክሃለን፤ አይዞህ እዚያ
ትሰነብታለህ”
“እሺ ንጉስ ሆይ” ብሎ ተሰናበተ
በነጋታው ወደ ህንድ ተላከ።
ንጉሱ እንደምንም ተጣጥረው ጸልየው፣ መልአከ ሞት ተገለጠላቸው።
ከዚያም
“ምን ልርዳዎት አላቸው”
“ልጄን አጫዋቼን ምን አጥፍቶ ነው መጥተህ ትኩር ብለህ ያየኸው?”
ሲሉ ጠየቁት፡፡ መልአከ ሞትም፡-
“ንጉስ ሆይ፤ እኔ ከአምላክ የታዘዝኩት ከህንድ አ ምጣው ተብዬ ነው፤
ኢየሩሳሌም ምን ያደርጋል ብዬ እኮ ነው” አለ።
* * *
ያለ ጥርጥር የተፃፈው ተፈጽሟል። መልአከ ሞትም ያንን አጫዋች ከህንድ
ሄዶ ወስዶታል ማለት ነው።
ምንም ቢሆን የ ተፃፈ ነ ገር ከመሆን አ ይዘልም። መ ቼም ቢሆን መ ቼም
እጣ ፈ ንታን ማ ለፍ የ ማይሆን መ ፍረምረም ነ ው። ጥ ብቁ ደ ራሲ ከ በደ
ሚካኤል፡፡
“እንዲሁም በዓለም ላይ አለ አንዳንድ ለነገር
በዚህ ቢሉ በዚያ ከመሆን የማይቀር”
ያሉት ይሄንኑ ሲያፀኸዩ ነው።
ሮበርት ብራውን የተባለው ገጣሚ እንዳለውም፡-
“ደሞም ማወቅ ማለት…ከውጭ ያለውን ሄዶ ከመፈለግ
ከውስጥ የበራውን እንዲወጣ ማድረግ” ይህ ንግግር ያባት ነው።
የሚጠብቀን ትግል እጅግ ሰፊና ከባድ ነው፡-
ከቀሳፊው ከኮረና ጋር ትግል !
ከትምህርት ውድቀት ጋር ትግል !
ከማህበራዊ ምስቅልቅል ጋር ትግል!
ከኢኮኖሚ ድቀት ጋር ትግል!
ልምድ ከሌለው ፖለቲከኛ ጋር ትግል!
ከውስጥና ከውጭ ወራሪ ጋር ትግል!
ከሙስና ጋር ትግል ወዘተ!
በተለይ ወጣቱ ላይ ካልተሰራና የስራ ዝግጁነቱ በአግባቡ ካልተደራጀ ዳግም ወደ ትናንትናዎቹ ተዋንያን መመለስ ግድ ይሆናል። ስለዚህ የወጣቱን
እውቀትና ንቃተ ህሊና ማሳደግ መሰረታዊ አቅም እንደሚፈጥር ያለአንዳች ዝንጋታ ትኩረት ሊደረግበት የሚገባ ተግባር ነው። ያልዘራነውን አናጭድም
ያላመረትነው አናፍስም ሁሉም ከባድ ጥረትና ትጋት የሚጠይቅ መራራ ትግል ነው። ሌላው ለኢኮኖሚው የሚሰጠው ትኩረት ማለት ነው።
በዚሁ ላይ የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ዛሬም ያልተረጋጋ መሆን አስጊ ነው! የመከላከያ ሀይል ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ እየተካሄደ ያለው ሁኔታ ምን
ይመስላል? ከጦርነቱስ በኋላ በህዝብ መካከል የሚኖረው ግንኙነትና ግንዛቤ ምን ይሆናል? የሚሉት በግድ መጠየቅ ያለባቸው ጉዳዮች ናቸው። በተለይ
ስለ ነገ አለማሰብ ቢያንስ የዋህነት ነው! “አረረም መረረም ማበሬን ተወጣሁ “ ማለት በአገር ጉዳይ ረገድ አያዋጣንም። እናስብ … እናስብ… እናስብ!


Read 12946 times