Print this page
Saturday, 09 January 2021 11:51

ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ ዛሬ ተማሪዎቹን ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት እንዲሁም በአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስፈርቱን አሟልቶ የተቋቋመው “ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ” በቢዝነስ ዘርፍ በደረጃ በጥራት ሲያስተምራቸው የነበሩትን ተማሪዎቹን ዛሬ ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ አትላስ አካባቢ በሚገኘው ማግኒሊያ ሆቴል ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመርቃል። የኮሌጁ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እሱባለው ታሪኩ ለአዲስ አድማስ እንደገለጹት የምረቃ ስነ-ስርዓቱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ታሳቢ ያደረገና በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር የወጣውን የተማሪዎች ምረቃ ፕሮቶኮል መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።
በዕለቱ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ጌታሁን ጋረደውን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ትምህርታቸውን በብቃት ያጠናቀቁ ተማሪዎችና፣ ወላጆቻቸው የትምህርት ባለሙያዎችና ትምህርት ላይ የሚሰሩ የግልና የመንግስት ተቋማት ሃላፊዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት የምርቃት ስነ-ስርዓቱ እንደሚካሄድም የኮሌጁ ዋና ስራ አስኪጅ ጨምረው ገልፀዋል።
ሃላፊው አክለውም በኮሌጁ ታሪክ የመጀመሪያ ሆነው ዛሬ ለለሚመረቁት ተማሪዎች በኮሌጁ የወደፊት የረጅም ጊዜ ራዕይ እና ጉዞ ፈር ቀዳጆች ናችሁና ምርቃታችሁ ታሪካዊ በመሆኑ አንኳን ደስ ያላችሁ በማለት ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Read 975 times