ከስፔናዊው ደራሲ ግሬሽያ ባልታሳር “The art of worldly wisdom” እና “The Hero” መፅሐፍት ተውጣጥቶ በኤፍሬም ጀማል “የብልህነት መንገድ” በሚል ወደ አማርኛ የተመለሰው መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ።
መፅሐፉ በቴዎድሮስ ሸዋንግዛው አርትኦቱ የተሰራለት ሲሆን ሰው ወደ ብልህት የሚወስዱትን መንገዶች የሚያብራራና የሚጠቁም ነው ተብሏል። በ187 ገፅ ተቀንብቦ በ150 ብር ለገበያ የቀረበው ይኸው መፅሐፍ በ”እነሆ” መፅሐፍት መደብር በዋናነት እየተከፋፈለ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።