Saturday, 16 January 2021 11:34

“እምዬ እና እቴጌ” የልጆች መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

      በያሬድ ሀይሉ (ምኒልክ ዳግማዊ) አዘጋጅነት የተሰናዳውና ልጆችን አዝናኝና ማራኪ በሆነ መንገድ እንዲያስተምር ታስቦ የተዘጋጀው “እምዬ እና እቴጌ” የልጆች መፅሀፍ ለንባብ በቃ መፅሀፉ ከቀለምና ከግራፊክስ ዲዛይን አመራረጡ ጀምሮ የአፄ ምኒልክንና የእቴጌ ጣይቱን ታሪክ ቀለል ባለ አገላለፅ እየተረከ እንዲሁም ከታሪኩ ጋር የሁለቱን ግለሰቦች ስዕል እያሰናኘ የተሰናዳ መፅሀፍ እንደሆነም ታውቋል፡፡
መፅሀፉ በቀለም፣ በምስልና በግራፊክስ ዲዛይን ማራኪ እንዲሆን ሰዓሊ ገብሬ ወርቁና ግራፊክስ ዲዛይነር ,ወሳኙ ተክሌ ከፍተኛ አስተዋእጾ እንዳደረጉም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በ75 ገፅ የተመጠነው መፅሀፉ በ75 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 4671 times