በደራሲ አዳነ ከተማ ተገኝ የተፃፈውና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው “ያልተለበሰው ካባ” ልብ ወለድ መፅፍ ባለፈው እሁድ ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከአፄ ሚኒሊክ መታሰቢያ ሙዚየም ጋር በአንኮበር ተመረቀ፡፡
ደራሲው ይህን መፅሀፍ ለመጻፍና ለንባብ ለማብቃት ከ30 ዓመታት በላይ በአዕምሯቸው ሲያብላሉት እንደነበር የገለፁ ሲሆን፣ ታሪኩ እውነት ቀመስ ሆኖ በተለይም በሰሜን ሸዋና አካባቢው ላይ መቼቱን አድርጎ፣ ባህልን፣ ታሪክን፣ ማንነትን እያሳየና ልብ እያንጠለጠል የሚነበብ ነው ተብሏል፡፡
የመፅፉ ምርቃት ከሙዚየሙ ምርቃት ጋር አንድ ላይ መካሄዱም መፅሀፉን ታሪካዊ ያደርገዋል ብለዋል ደራሲው፡፡ በ311 ገፅ የተቀነበበው መፅሀፉ፣በ150 ብርና በ30 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡
Saturday, 16 January 2021 11:12
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና