Tuesday, 19 January 2021 00:00

“በክርክር እና በወይይት የማሸነፊያ ስልቶች” የተሰኘ መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በደራሲ ሲሳይ አሰፌ ተሰማ የተሰናዳውና ክርክርን በተለያዩ አወዶች ማሸነፍ የሚቻልበትን የሀሳብ ልዕልና እና ጥበባዊ አቀራረብ የሚያመለክተው” በክርክርና በውይይት የማሸነፊያ ስልቶች”  የተሰኘ መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
መፅሀፉ በዋናነት ክርክር ጠብ ወይም ግጭት አለመሆኑን ይጠቅስና፣ በቤተሰብ፣በጓደኛሞች በተለያዩ ቡድኖች፣ አጭር ወይም ለረጅም ጊዜ ለተለያየ ዓላማ በተቋቋሙ ኮሚቴዎች፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መካከል ክርክርና ውይይት በሚካሄድበት ጊዜ ለማሸነፍ ምን ዓይነት ጥበቦችና ስልታዊ አቀራረቦችን መጠቀም እንዳለበት አቅጣጫ ይጠቁማል ተብሏል፡፡
በተለይም በማህበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊና በፖለቲካ ጉዳዮች  ላይ ለሚከራከሩና ለሚወያዩ አካላት ግባቸውን ለማሳካት ይህ መፅሀፍ እንደዋና መሳሪያ ሊያገለግል እንደፈሚችል ደራሲው ጠቁመዋል፡፡
በ244 ገፅ የተቀነበበው መፅሀፉ በ180 ብርና በ15 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 6973 times