Saturday, 16 January 2021 12:14

ብልጽግና 10 ሚሊዮን አባላት አሉኝ አለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)

   የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ  ቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ትናንት ባቀረበው የ6 ወር የስራ አፈፃጸም ሪፖርት፤ በአሁኑ ሰዓት በመላው አገሪቱ የተመዘገቡ 9 ሚሊዮን 941 ሺህ 467 አባላትና አመራሮች እንዳሉት አስታውቋል፡፡
የፓርቲው የማዕከላዊ ቁጥጥር ኢንስፔክሽን ኮሚሽን በሸራተን ሆቴል በተደረገው የብልጽግና ፓርቲ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ ባቀረበው በዚህ ሪፖርቱ፤ መዋቅሩን በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች በመዘርጋቱ ነው ብሏል፡፡
አስር ሚሊዮን ገደማ አመራርና አባላትን በመላ ሃገሪቱ ያፈራው ብልጽግና፤ በአሁኑ ወቅት ውስጣዊ ድርጅታዊ አንድነቱን በማጠናከር ተግባር ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ በቀጣዩ ምርጫም በመላ ሃገሪቱ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ መቅረብ የሚያስችሉትን የምርጫ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑም በመድረኩ ተወስቷል፡፡
በኢህአዴግ ፍራሽ ላይ የተመሰረተው ብልጽግና፤ በሃገሪቱ ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርአትን ለመገንባት ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ አላማና ግብ ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በተደጋጋሚ ይገልፃል፡፡

Read 12018 times