Saturday, 23 January 2021 14:42

“ግድቡ የኔ ነው” የስዕል አውደ ርዕይ ዛሬ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ስዕሎች ለእይታ የሚቀርቡበት “ግድቡ የኔ ነው” የተሰኘ የስዕል ዐውደ ርዕይ ዛሬ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በሀያት ሬጀንሲ ሆቴል ይከፈታል። 6 ሰዓሊያን ከህዳሴው ግድብ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ሰአሊያኑ ብሩክ የሺጥላ ፣ብርሃን በየነ፣ ሜሮን ኤርሚያስ፣ እስራኤል ወ/ገብርኤል፣ ኤፍሬም ተፈራና ሰለሞን ግዛው ስእሎቹ በሙሉ የህዳሴው ግድብ ላይ ትኩረት እድርገው የተሰሩ ሲሆን ፣እያንዳንዱ ሰዓሊ 5 ስራዎችን እንደሚያቀርብና በአጠቃላይ 30 ስዕሎች ለእይታ እንደሚበቁ ሰዓሊ ብርሀን በየነ ገልፃለች፡፡
አውደ ርዕዩ እስከ ሰኞ ጥር 17 አመሻሽ ድረስ ለእይታ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡



Read 765 times