Saturday, 23 January 2021 14:56

“ደራሲያን በሀገር ፈተና ወቅት” በሚል ርእስ ውይይት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


           አንጋፋው ደራሲያን ማህበር የተመሰረተበትን 60ኛ ዓመት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ “ደራሲያን በሀገር ፈተና ወቅት” በሚል ርዕስ ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቤተ መፅሀፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል፡፡
በዚህ ውይይት ላይ የኢትዮጵያ ደራሲያን ባለፉት 60 ዓመታት ያለፈበትን ውጣ ውረድ የሚያሳይ ጥናታዊ ፅሁፍ በደራሲ ጌታቸው በለጠ የሚቀርብ ሲሆን ጋዜጠኛና ደራሲ ጥበቡ በለጠ ደግሞ “ ደራሲያን በሀገር ፈተና ወቅት” በሚል ርዕስ ጥናት እንደሚያቀርቡ የማህበሩ ፕሬዚዳንት ደራሲና ባለቅኔ አበረ አዳሙ ተናግረዋል፡፡ በማህበሩ የወደፊት ጉዞ ላይም ውይይት የሚካሄድ ሲሆን ግጥሞችና ሌሎችም ጥበባዊ መሰናዶዎች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡


Read 11483 times