Saturday, 23 January 2021 14:55

“ ለሀገር ፈውስ ኢትዮጵያዊነት ይመለስ” የጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በምስክር ጌታቸው ሚዲያና ፕሮሞሽን በየወሩ የሚካሄደው የኪነ-ጥበብ ምሽት የዚህ ወር መሰናዶ “ለሀገር ፈውስ ኢትዮጵያዊነት ይመለስ”  በሚል ርዕስ የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በምሽቱ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ ፣ሙአዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣በድሉ ዋቅጅራ(ዶ/ር)፣ የሙዚቃ ባለሙያ ሰርፀ ፍሬ ሰብሀትና ደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደ ዲስኩር ያቀርባሉ። በደራሲ አንዱአለም አባተ (የአፀደ ልጅ) መነባነብ፣በገጣሚና ጋዜጠኛ ተፈሪ አለሙና በገጣሚ ቃልኪዳን ሙሉጌታ ግጥም፣እንዲሁም በመምህር እፀገነት ከበደ ወግ እንደሚቀርቡና መሰናዶው በሙዚቃ እንደሚታጀብ ታውቋል፡፡ የመግቢያ ዋጋ 100 ብር ሲሆን የመግቢያ ትኬቱ በጃፋር ዓይናለምና ዮናስ መፃሕፍት መደብሮች፣ በጣይቱ ሆቴል፣ ካዛንቺስ በሚገኘው ጆሲ ልብስ ስፌት ቤት ይገኛል ተብሏል፡፡

Read 11480 times