Saturday, 23 January 2021 14:59

የታገል ሰይፉ “ተልባና ጥጥ” በገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  በገጣሚና ደራሲ ታገል ሰይፉ የተፃፈው “ተልባና ጥጥ” የተሰኘ ረዥም ልብወለድ መፅሐፍ ሰሞኑን በገበያ ላይ ዋለ። “ደማልቦ” የሚባል ወረርሽኝ አዲስ አበባ ውስጥ ቢገባ ምን እንደሚፈጠር ምናባዊ በሆነ አቀራረብ የሚተርከው ልቦለዱ፤ በ243 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ200 ብር እየተሸጠ ይገኛል።
ደራሲው ከዚህ ቀደም “ፍቅር” (1982)፣ “ቀፎውን አትንኩት” (1986)፣ “ሌዋታን” /ኢሃዲግ ካንፕ ውስጥ የተገኘው አውሬ/ ልቦለድ (1989)፣ “የሃምሳ አለቃ ገብሩ ታሪኮች” (1990)፣ “የሰዶም ፍፃሜ” (1996)፣ “በሚመጣው ሰንበት” (2005)፣ “ብስጦሽ ቁዋጭ ቁዋጣሽ ቆር” /ልቦለድ/ (ጥቅምት 2012)፣ “የእንቅልፍ ዳር ወጎች /ተረቶች/” (ሐምሌ 2012) ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል።


Read 12321 times