Saturday, 30 January 2021 10:35

ፖሊስ ባልደራስ ለነገ የጠራው ሰልፍ ተቀባይነት የለውም አለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

  ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ፤ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ዘር ተኮር ጥቃት  እንዲቆም መጠየቅን ጨምሮ በ4 ዋኛ ጉዳዮች ላይ ለእሁድ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ተቀባይነት እንዳላገኘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ባልደራስ በዋናነት ዘር ተኮር ጥቃትን ለመቃወም፣ የታሰሩ አመራሮቹ ከእስር እንዲፈቱ ለመጠየቅ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ የሚያካሄደውን የህንፃዎች ግንባታ በመቃወም እንዲሁም ለሱዳን ወረራ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ለመጠየቅ ያለመ ሰላማዊ ሰልፍ ነገ እሁድ አቅዶ ነበር።
ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ትናንት በሰጠው መግለጫ፤ ሰልፉ ተቀባይነት እንዳላገኘ አስታውቋል ብሏል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት አስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ፤ ጥር 18 ፤ ለባልደራስ በፃፈው ደብዳቤ፤ ሰልፉ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ተቀባይነት አለማግኘቱን ጠቅሶ ምላሽ መስጠቱን ፖሊስ በመግለጫው አመልክቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ሰልፉ ይደረጋል ተብሎ እየተላለፈ ያለው መልዕክት ህገ-ወጥ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ፤ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት ላይ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን ፖሊስ  አስታውቋል።

Read 705 times