Saturday, 30 January 2021 10:44

በፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው ኢሶዴፓ ከመድረክ ራሱን አግልሏል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

 መድረክ የአራት ፓርቲዎች ስብስብ ሆኖ ይቀጥላል

            በፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ከመድረክ የፖለቲካ ስብስብ ራሱን ያገለለ ሲሆን መድረክ  የአራት ፓርቲዎች ስብስብ ሆኖ ይቀጥላል ተብሏል።
የመድረክ መስራች አባል የሆነው ኢሶዴፓ፤ ከመድረክ ለመለየት የተገደደው ከኦፌኮ ጋር እየተፈጠረ በመጣው የሃሳብና የአካሄድ ልዩነት  ምክንያት ነው ያሉት ምንጮች፤ በመድረክ መተዳደሪያ ደንብ መመራት ስላልተቻለ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡
ምርጫ እንዴት ይካሄድ? የሽግግር መንግስት ይቋቋም  በሚሉትና ኦፌኮ ከመድረክ እውቅና ውጪ  ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር  ጥምረት እየፈጠረ መሆኑ እንዲሁም ከመድረኩ እውቅና ውጪ መግለጫዎች የመስጠት አካሄድ መከተሉ አብሮ የሚያስቀጥል አልሆነም ብሏል ኢሶዴፓ።
የኢሶዴፓን ከመድረክ መለየት ለአዲስ አድማስ ያረጋገጡት የኦፌኮ ዋና ፀሃፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ፤  የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለመግባባት መለያየት በአገሪቱ የተለመደ ነው፤ ኢሶዴፓ ከመድረክ መለየቱ መድረክ ላይ የሚፈጥረው ጉልህ ተፅዕኖ የለም ብለዋል።
መድረክ አሁንም የአራት ፓርቲዎች ስብስብ ማለትም የአረና፣ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ፣ የኦፌኮ እና የአፋር ነፃነት ፓርቲ ስብስብ ሆኖ ይቀጥላል-ብለዋል አቶ ጥሩነህ።
ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችም መድረክን ለመቀላቀል ጥያቄ አቅርበዋል፣ ሂደቱ ሲጠናቀቅ  ማንነታቸው ይፋ ይደረጋል ብለዋል አቶ ጥሩነህ ለአዲስ አድማስ በሰጡት መግለጫ።

Read 921 times