Saturday, 30 January 2021 10:49

እነ አቶ ልደቱ አያሌው ህብር ኢትዮጵያን ወክለው በምርጫ ይወዳደራሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

   በምርጫ ቦርድ የፓርቲ ዕውቅናቸው የተሰረዘባቸው የኢዴፓና ኢሃን አመራሮችና አባላት  ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን እንደተቀላቀሉ የተገለፀ ሲሆን  በቅርቡ ከእስር የተለቀቁት አቶ ልደቱ አያሌውና ኢ/ር ይልቃል ጌትነትም ተጠቃሾች ናቸው፡፡
የኢዴፓ መስራችና አመራር የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌውና የኢትዮጵያ ሃገር አቀፍ ንቅናቄ(ኢሃን) ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በትናንትናው ዕለት በህብር ኢትዮጵያ ጽ/ቤት ተገኝተው የአባልነት ፎርም መሙላታቸውን የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ግርማ በቀለ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡
እነ አቶ ልደቱን ጨምሮ በሁለቱ ፓርቲዎች ውስጥ የነበሩ አባላትም  ህብር ኢትዮጵያን ወክለው በቀጣዩ ምርጫ የሚወዳደሩ ሲሆን በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ወደ ከፍተኛ አመራር የሚመጡ አዲስ ተመዝጋቢ አባላት እንደሚኖሩ ነው አቶ ግርማ የጠቆሙት፡፡
ፓርቲው ከ280 በላይ በሚሆኑ የምርጫ ወረዳዎች ላይ እጩዎችን ማዘጋጀቱንና በቀሪዎቹ ቦታዎች ላይም እጩዎች እየመለመለ መሆኑን የጠቆሙት የህብር ሊቀመንበር አቶ ግርማ አቶ ልደቱና ኢ/ር ይልቃልን ጨምሮ አዳዲሶቹ አባላትም ለምርጫ በእጩነት እንደሚቀርቡ አስረድተዋል፡፡

Read 12961 times