Saturday, 06 February 2021 13:42

“ኩርመኝ” መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     የደራሲ ውብሸት በቀለ የመጀመሪያ ስራ የሆነው “ኩርመኝ” የተሰኘ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡
መፅሐፉ ደራሲው ከልጅነቱ ጀምሮ አያቱ ይነግሩት የነበሩትን ተረቶችና የልጅነት ጊዜው ላይ የተመሰረቱ ታሪኮችን ቀምሮ ማሰናዳቱን በመግቢያው ላይ  አስፍሯል።
በልጅነት ታሪክ ላይ የተመሰረተው መፅሀፉ፣ በዘጠኝ ዋና ዋና ምዕራፎች ተከፋፍሎ፣ በ152 ገጾች  የተቀነበበ ሲሆን በ120 ብር ለገበያ ቀርቧል።

Read 11431 times