የደራሲ ውብሸት በቀለ የመጀመሪያ ስራ የሆነው “ኩርመኝ” የተሰኘ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡
መፅሐፉ ደራሲው ከልጅነቱ ጀምሮ አያቱ ይነግሩት የነበሩትን ተረቶችና የልጅነት ጊዜው ላይ የተመሰረቱ ታሪኮችን ቀምሮ ማሰናዳቱን በመግቢያው ላይ አስፍሯል።
በልጅነት ታሪክ ላይ የተመሰረተው መፅሀፉ፣ በዘጠኝ ዋና ዋና ምዕራፎች ተከፋፍሎ፣ በ152 ገጾች የተቀነበበ ሲሆን በ120 ብር ለገበያ ቀርቧል።