Print this page
Saturday, 11 August 2012 14:21

የዓለም ወይን - ጠጪዎች ተባበሩ! (Wine Drinkers of the World Unite!)

Written by  ትርጉም- ነቢይ መኮንን
Rate this item
(0 votes)

ክርስቶፈር ሒቸንስ

አንድ እንደዋዛ የሚነገር ቁም ነገር አለ፡፡ ወደ አንድ የተወሰነ ቡና ቤት ትገቡና ከጓደኞቻችሁ ጋር
ጨዋታ ትጀምራላችሁ፡፡ በመካከል አስተናጋጁ ይመጣና፤
“ምን ልታዘዝ?” ይላል፡፡
“ቢራ!”  ትሉታላችሁ
“ምን አይነት?” ይላችኋል፡፡
“እንደ ሆነው፤ የተመቸህን” በመሰላቸትና ጨዋታችሁን ለመቀጠል ስለጓጓችሁ ነው፡፡
“በደሌ ነው ሜታ?” ይላል እንደገና
“ኦ! በቃ ሜታ አድርገው”
“ትልቁን ነው ትንሹን?”
አሁን ትዕግሥታችሁ ያልቅና “እየው፤ ከእንግዲህ ወዲያ አንድ ጥያቄ ትጠይቀኝና ማንጋጭሌህን ነው
የማወልቀው!”
“የት? እዚህ ነው እውጪ???”
እንዲህ ልባችሁን የሚያወልቅ ቦይም (አስተናጋጅም) አለ በአገራችን!
***
ትላንት ማታ በአንድ መካከለኛ ሬስቶራንት ከጓደኞቼ ጋር ራት እየበላን ጨዋታ ቀጥዬ የምሽቱ ቁንጮሆኜ ነበር! ሆኖም እንደማንኛውም ወሰን-የለሽና ካቅም በላይ ጉጉት፤ ዋናው ቁም ነገሬ ላይ ደርሼላጠናቅቅ ስል፤ እጅግ አስገራሚ ነገር ተከሰተ፡፡ አንድ አስተናጋጅ ድንገት መጣ፡፡ በትከሻዬ ላይዘመም ብሎ በንግግራችን መካከል አቋርጦ ቢላና ሹካ አነሳ፡፡ ከዚያ ምግቤን መቆራረጥ ቀጠለ፡፡ የዚህዋልጌ ፀባይ መነሻ ምንም ጭብጥ የለውም፡፡ ከመሄዳችሁ በፊት ላግዛችሁ ዓይነት ስሜት ሳይታይበት፤የቆራረጣቸውን ክፍልፋዮች በሌሎቹ የምግብ አጋሮቼ ሣህን ላይ መደልደል ጀመረ፡፡ የለም፡፡ ለነገሩዋና ነገር ያ ብቻ አይደለም፡፡ ያደረገው ነገር  ምን መሰላችሁ? የውይይታችን ነገር ዋንኛ ቁም ነገርየሆነውን ብርቅ ጨዋታና የነብስን ፍሰት አቋርጦ /አነቅፎ፤ በላዬ ላይ ዘሞ፣ በጠረጴዛው ማህልተቀምጦ የነበረውን የወይን ጠርሙስ አንስቶ፤ በየአንዳንዱ ሰው ብርጭቆ ላይ ማርከፍከፍ/መቅዳትነበር! እኔ ለማወቅ የፈለኩት ደግሞ፡- እንዲህ ያለ ኋላ ቀር ባህል እንዴት ሥር ሰዶ እግሩን ሊተክልቻለ? እኛስ እንዴት ብለን ልንቀበለውና ልንቀጥልበት ቻልን?አንድ ሬስቶራንት መጥፎ መስተንግዶ በደምበኞቹ ላይ የሚጭንባቸው ሁለት መንገዶች አሉ፡፡አንደኛው ምግቡ እስኪመጣ እንድንትጠብቅ በማድረግ፣ የሠራተኞቹን ዐይን ለማየት እንዲያዳግትናእንዲያፍሩ ማድረግ ነው፡፡(አንድ ጊዜ፤ ልጄ ገና የአምሥት ዓመት ልጅ ሳለ፤ ምግቡ እስኪመጣ ስንጠብቅ “እነዚህ ሰዎች
ለምንድነው “ዌይተርስ” የሚባሉት? የምንጠብቀው እኛ አደለን እንዴ? ብሎ ጠይቆኛል)ሁለተኛው መንገድ ደግሞ በፈጠጠ ሁኔታ ጣልቃ መግባት ነው፡፡ የቤቱን “ልዩ ምግብ” ዝርዝርበረዥሙ በመተንተንና ምን ዓይነት ይሁንልዎት ዓይነት የአዛኝ ቅቤ አንጓች ጥያቄ መደርደር፡፡ አንድኒውዮርከር መጽሄት ላይ የወጣ ካርቱን ትዝ ይለኛል፡፡ ባልና ሚስት ፍቅረኛሞች ሊተኙ አልጋ ላይወጥተዋል፡፡ ድንገት ስልክ ሲደወል ባል ያነሳል፡፡ የስልኩን አፎት በመዳፉ ከድኖታል፡፡ “የደወልነውራት ከበላችሁበት ሆቴል ነው፡፡ እስካሁን ደስ እንዳላችሁ መቀጠላችሁን የሆቴል ቤቱ ባለቤትለማወቅ ስለፈለጉ ነው!” ይላል ፅሁፉ፡፡ድንገት መጥቶ የወይኑን ቡሽ ከፍቶ በየብርጭቆው ላይ ማንደቅደቅ የዋልጌ ባህሪ ቁንጮ ብልግናነው፡፡ ትንፋሽ-ጨራሽ የብልግና ተግባር መሆኑ ብቻ ሳይሆን ግልጥጥና ፍጥጥ ያለ የቅጥረኝነትመልዕክት አለበት፡- “ቶሎ ቶሎ ጠጡና ሌላ እዘዙዋ!” የሚል፡፡ በዚህ ዓይነቱ ብልግና መዋረዳችንናመደንዘዛችን ዕውነት ነው፡፡ እንዲያውም እኔ ያየሁዋቸው አንዳንድ አስተናጋጆች የሚገርሙ ናቸው፡፡ሰው እየተጫወተ ማህል ገብተው ፋሽኮውን ያነሱና የመጨረሻዋን ጠብታ አንጠፋጥፈው ሲያበቁበዓይን አውጣነት “ሌላ ይጨመር?” ይላሉ፡፡ እንግዲህ ይሄንን ዓይነቱን ነገር ምግብ ላይ ሲፈጽሙትእንዴት እንደሚሰቀጥጥ ይታያችሁ፡፡ብዙ ሰው የኔን ያህል ወይን የሚወድ አይመስለኝም፡ብዙ ሴቶች ከምግብ ጋር አንድ ብርጭቆ ወይምግማሽ ብርጭቆ ወይን ይጠጣሉ፡፡ ምን የመሰለው ወይን በማይጠጣ ሰው ብርጭቆ ላይ ሲቀዳ ሳይነርቬን ነው የሚነካው፡፡ላይቀምሱት ወይም ከናካቴው ላይፈልጉትም ይችላሉ፡፡ ራቱ ሲያልቅ ወይኑ እዚያው ብርጭቆውውስጥ እንደነፈሰበት ይቀራል፡፡ ሚስተር ኮልማን የተባለው ባለሬስቶራንት የከበረው በአግባቡከተበላው ሰናፍጭ ክፍያ ሳይሆን ከየገበታው በሚተርፈው ሰናፍጭ ነው ይባላል! ሬስቶራንቶች ገቢለማስገባት በሚል ምግቡን ማብከንከንን እንደሙያ መያዝ የለባቸውም፡፡ ይሄም አንዱ የብልግናጠርዝ ነው፡፡ዋናው ጉዳይ ትርፍ ማግበስበሱ ነው፡፡ እኔ ብሆን ደጋሹ ብዬ ሳስበው ዝግንን ይለኛል፡፡(“ብርጭቆዎትን እንደገና ልሙላልዎ? ይሄን ወይን ይሞክሩት የርሶ ጣዕም ሊሆንይችላል?”)
እንደደጋሽ ብቻ ሳይሆን እንደእንግዳም ብሆን የተዋረድኩ መስሎ ነው የሚሰማኝ፡፡ ምክንያቱም ራትላይ የሚጥም ጨዋታ ስፈልግ አንድ ሰውአቋርጦኝ አላስፈላጊ ጠያቄ ሲጠይቀኝ ንዴቴ ይታወቀኛልናነው፡፡ እያንዳንዱን ሰው ከሚወተውትና ከሚጠይቅ በጨዋ ደንብ አብሮን ቢቀመጥ ይሻለዋል፡፡ ነርቭየሚነካ ነገር!ይሄን ሁሉ ለምን ለመታገስ በቃን ወደሚለው እንመለስ እስቲ፡፡እንደሚመስለኝየወይንንንግድማስፋፋትና(Business) እና የገቢ ዋስትና ማጣትን በተመለከተ የተደቀነው ችግር ነው ዋናውጣጣ፡፡ የወይን አስተናጋጅ በራሱ ሙያ ትልቅ ነኝ ባይ ነውና ስለወይን የማያውቁ ተስተናጋጆች ላይትንሽ የበላይነት የማሳየት ፈሊጥ ሳይኖረው አይቀርም፡፡
ያ ደሞ ደምበኞችን ማሸማቀቁ አይቀርም፡፡
ወደ አንድ የከተማው ምስኪንና ደካማ ግሮሰሪ ብትሄዱ፤ ወይን በጣም ውድ መሆኑን ታያላችሁ፡፡ምክንያቱ ሌላ እንዳይመስላችሁ፤ የበለጠ ዋጋ ማውጣት አለበት ብለው ስላሰቡ ብቻ ነው፡፡ ከዛየልማድና የሱስ ጉዳይ ደሞ ይከተላል፡፡ ለነዚህ ሬስቶራንቶች ደምበኞቻቸውን በዚህ ጋጠ - ወጥ
መንገድ የመግፋት መብት እንዲኖራቸው አድርገናቸዋል፡፡ግን ልብ እንበል፡፡ የሚያስፈልገው ትንሽ መከላከል ነው፡፡ አንፈልግም፣ እምቢ ማለት ነው
በዋሺንግተን በጆርጅ ታውንና በዲፕሎማቲክ ራት ላይ ጋባዡ ወይዛዝርቱ እንደበቃቸው ሲገምትጥለው እንዲወጡ መጠየቁ የተለመደ ነበር፡፡ወንዶቹ የተለመደ መጠጣቸውን እየጠጡ፣ ሲጋራቸውንእየማጉ ታላላቅ የመንግሥት ጉዳዮችን እያወጉ እንዲቀመጡ ይተውዋቸዋል፡፡ ሴቶቹን ግን እንዲወጡይጋብዟቸዋል፡፡ እንግዲህ ይህ ተዘውትሮ ባለበት ጊዜ፣ አንድ ምሽት/በ1970ዎቹ፤ በብሪቲሽ ኤምባሲ፤የቀድሞዋ ካቴሪን ግርሃም ወይኑን ትታ እንድትሄድ ስትጠየቅ አሻፈረኝ አለች፡፡ ማንም ሊያስገድዳትአልቻለም፡፡ በአንድ ቀን ውስጥ ወሬው ተዛመተና በአጭር ጊዜ ውስጥ ያንን የጅል ተግባር ሰው ሁሉእርግፍ አድርጐ ተወው!ሥልጣኔን የተፋጠጡ፣ ከዚህ የከፉ ችግሮች እንዳሉ አጥቼው አይደለም፡፡ ከዚያ የከፉ ከባባድየሰብዓዊ መብት መጣሶችና መዳፈሮችንም ሳላቅ ቀርቼ አይደለም፡፡ ይሄ ከላይ ያወራሁላችሁ ነገር ግንበአንድ ምት፤ ፀጥ - እርጭ ልናደርገው የምንችለው ጉዳይ ነው! ወደፊት፤ ማንም ጨዋታችሁንከሰውነታችሁ ጋር የሚያዋህድ ምግብ ላቀርብ ነው በሚል ጮሌነት የሂሳብ ደረሰኙ እንዲደልብየሚያደርግ ሰው ካጋጠማችሁ በጣም ትሁት ሁኑለት፤ ግን ደሞ ጥብቅ ሁኑ፤ ያን አንፈልግም ተወንብላችሁ እቅጩን ነግራችሁ ካጠገባችሁ አስወግዱት! (ስሌት መጽሔት፣ ሜይ 26 2008)የተርጓሚው ማስታወሻእንደ ፈረንጆች በወይን አቀዳድ ላይ እንወያይ ብል ቅንጦት ይመስለኛል፡፡ ሆኖም እኛ በተለያዩ
የአስተናጋጅ ዓይነቶች መቸገራችንን አናጣውምና ደራሲው አንድ ትልቅ ቁም ነገር ያስጨበጠንይመስለኛል፡-ስለ ትንንሾቹ ጉዳዮች ለመብታችን መቆርቆር ከቻልን ወደ ትልልቆቹ መብቶቻችን ጥያቄዎች መሸጋገርእንችላለን - “ሳንቲሞቹን ጠብቁ ብሮቹ ራሳቸውን ይጠብቃሉም” የሚል መንፈስ ውስጡ አይጠፋም!(Take Care of the Penies, the dollars will take care of themselves እንዲሉ)ግዴታ እንጂ መብት የሚገባን ስንቶቻችን ነን?አንድ ታክሲ ውስጥ አንድ ሰው “ትርፍ ለሚቀመጥ ሰው ቦታ አልለቅም፡፡ ሰውዬውንበደግነትማስቀመጤሳይሆንጠቃሚው፣ እኔ መብቴን ማወቄ፣ ማስከበሬና ለባለታክሲዎች ስግብግብአትራፊነት አለመገዛቴ ነው!” ይላል ፍርጥም ብሎ፡፡ በእምቢታው ፀና! ታክሲው ሄደ ሄደና ይህ  ሰውወረደ፡፡ ታክሲው ውስጥ ጉምጉምታ ሆነ! የጉምጉምታው መንፈስ “እንዲህ ቅርብመውረዱላይቀርምናለሰውየውንበትርፍቢያስቀምጠው?!” አለ፡፡ ከመሀል አንድ ሁኔታውን የታዘበ ተሳፋሪ “እዚህ
አገር መንግሥት አደለም፤ ህዝቡ ነው ፋሺስት!” አለ እየወረደ፡፡ ይሄንን እንጠያየቅ!ስንቶቻችን ነን መብት እሚገባንና ለመብት መቆርቆር መብት መሆኑን የምናውቅ? ፈረንጆቹ I’m atax payer የሚሉት ፈሊጥ አላቸው፡፡ እኛ አገር ከከባድ እስከ ቀላል ግብር የማይከፍል ሰው የለም -
በየመልኩ! ግብር የከፈልኩበትን ዋጋ አምጡ፣ ሥልኬን ሥሩ ወዘተ. የምንል ስንቶቻችን ነን? ኧረስለመብት እንነጋገር፣ እንወያይ፣ እንወሳሰን!!

 

 

 

Read 1562 times Last modified on Saturday, 11 August 2012 15:30