Saturday, 06 February 2021 14:33

ዛጎል

Written by 
Rate this item
(6 votes)

ከጠንካራው ልብሷ
ከውስጥ ከመንፈሷ
ውጪ ተስፈንጥሮ ከጉንጮቿ የኖረ
ጥቁር ምልክት ከፊቷ ነበረ
ከዛጎል ልቧ ላይ
ከሴትነቷ ላይ
የማጣትን ሸማ እየፈታተለ
ወጣትነት አልፎ እርጅና አየለ
ይኸው ምልክቷ
የትላንት ጉዞዋን፣ በግልጽ የሚናገር
ያለፈውን ሁሉ፣ በመዳፍ የሚሰፍር
ከአይኖቿ በታች፣ ጥቁር ጽህፈት አለ
መለያ ምልክት፣ ይኸው እየመሰለ
ማድያት አኑሮ፣ ውበቷን ሰውሮ
ከማጣት ሀሳቧ፣ ዛጎል ልቧን ትቶ
ካዘነው ልቧ ጋር፣ ፊቷ ላይ አምታቶ
ማዲያት አኖረ
ውበቷን ሰወረ
ማጣቷን ዘከረ።
(“የሱናማዊቷ ቃል” ከተሰኘው የገጣሚ ዋዜማ ኤልያስ የግጥም መድብል የተወሰደ)



Read 2970 times