Saturday, 13 February 2021 11:07

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው የኑሮ ውድነቱን እንደሚያባብሰው ተገለፀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ6 ወራት ብቻ በነዳጅ ዋጋ ላይ ከ4 ብር በላይ ጭማሪ ተደርጓል
    
           የንግድ ሚኒስቴር በመላው ኢትዮጵያ በነዳጅ ምርቶች ላይ  ባደረገው የዋጋ ማስተካከያ፤ የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ ከ23 ብር ከ67
ሳንቲም ወደ 25 ብር ከ82 ሳንቲም ከፍ ማለቱ ታውቋል። ጭማሪው የኑሮ ውድነቱን እንደሚያባብሰው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች
ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚያደርገው የዋጋ ጭማሪ እያደገ መጥቷል።  በያዝነው ዓመት ብቻ
በነዳጅ ዋጋ ላይ በሊትር የአራት ብር  ጭማሪ አድርጓል። የነዳጅ ዋጋ በ1998 ዓ.ም ከነበረበት በሊትር 6.57 ሳንቲም በአሁኑ ወቅት ከአራት እጥፍ
በላይ አድጎ 25 ብር ከ82 ሳንቲም ደርሷል።

Read 1918 times