Saturday, 13 February 2021 11:19

“በትግራይ ጦርነት 83 ንፁሃን ተገድለዋል” ሂውማን ራይትስ ዎች

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

 “ንፀኃንን ኢላማ ያደረገ ጥቃት አልተፈፀመም” - መንግሥት
               
           በትግራይ በተካሄደው ጦርነት 83 ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸውን ሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርት አድርጓል፡፡
አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይት ዎች መንግስት በትግራይ ያካሄደውን ህግ የማስከበር ዘመቻ አስመልክቶ አከናውኘዋለሁ
ባለው ምርመራ 83 ንጹሃን በመንግስት ሃይሎች በተተኮሰ መሳሪያዎች ተገድለዋል ብሏል፡፡ ከ300 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን አመልክቷል።
በመቀሌ፣ ሽሬና ሁመራ አካባቢዎች መኖሪያ ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ ት/ቤቶችና የገበያ ቦታዎች የጥቃት ኢላማ ተደርገዋል የሚለው የሂውማን
ራይትስ ዎች ሪፖርት ለመጀመሪያዎቹ የጦርነት ቀናት የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ንፁሃንን ባለየ መልኩ ከባድ መሳሪያዎች ሲታኮሱ ነበር
ብሏል፡፡
በአሁን ወቅትም በትግራይ የምግብ፣ መድሃኒት፣ የህክማናና የመገኛኛ አውታሮች ችግር መኖሩን ሂውማን ራይትስ ዎች ከትናንት በስቲያ ይፋ
ባደረገው ሪፖርት አትቷል፡፡
ሂውማን ራይትስ ዎች ይህን ምርመራ ያከናወነው በተለይ በመቀሌ፣ሁመራና ሽሬ አካባቢዎች 37 የአይን ምስክሮችን፣ዘጠኝ ጋዜጠኞችን፣
የረድኤት ሰራተኞችንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን አነጋግሮ መሆኑን ያስገነዘበ ሲሆን በግጭቱ ላይ የመንግስት ወገን ምላሽ በማጣቱ
እንዳልተሳካለት አትቷል፡፡ ጉዳዩ በተባበሩት መንግስታት እንዲጣራ ጠይቋል።
ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ ከወራት በፊት በትግራይ ስለተካሄደው የህግ ማስከበር ሂደት ላይ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባቀረቡት ማህበራዊ
የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት እንዳልፈፀሙ እና በጦርነቱ ሰላማዊ ዜጎች እንዳልሞቱ መግለፃቸው አይዘነጋም፡፡

Read 13428 times