Saturday, 13 February 2021 12:32

“እስከ መቼ” የኪነ-ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

      ባለፈው ሳምንት ሰኞ ሊካሄድ የነበረውና በአቅራቢዎች ድንገተኛ ችግር ምክንያት የጊዜ ለውጥ የተደረገበት “ እስከ መቼ” የኪነ-ጥበብ ምሽት ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል ይካሄዳል።
በጉዞ ሚዲያና ማስታወቂያ በየወሩ የሚሰናዳው “ብራና” የኪነ-ጥበብ መሰናዶ የዚህ ወር ዝግጅቱ “እስከ መቼ” የሚሰኝ ሲሆን በዕለቱ አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ፣ አርቲስት ዓለምፀሀይ ወዳጆ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ፣ አርቲስት አስቴር በዳኔ፣ ደራሲና ገጣሚ አንዱዓለም አባተ (የአፀደ ልጅ) ፣ ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም፣ አርቲስት ደሳለኝ ስዩምና ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወግ፣ ዲስኩርና ግጥም እንደሚያቀርቡ የመርሃ ግብሩ አዘጋጅና የመድረኩ አጋፋሪ ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ ገልጿል።
በዕለቱ ድምፃዊ ካሳሁን እሸቱ ከሻሎም አቢሲኒያ ሙዚቃ ቡድን ጋር መድረኩን የሚደምቅ ሲሆን የመግቢያ ዋጋው 100 ብር እንደሆነም ታውቋል።

Read 13302 times