Saturday, 13 February 2021 12:34

የቢኒያም ወርቁ “ህያው ብራና” መፅሐፍ ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የአርቲስት ቢንያም ወርቁ “ህያው ብራና” መፅሐፍ ሰኞ የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በጊዮን ሆቴል ይመረቃል።
በዕለቱ በመፅሐፉ ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን አጭር ተውኔት በአርቲስት ሰለሞን ቦጋለና ሳምሶን ታደሰ (ቤቢ)፣ ወግ በአርቲስት ፍቃዱ ከበደ፣ ግጥም በሰለሞን ሳህለ ትዕዛዙ፣ ደምሰው መርሻ፣ አስታውሰኝ ረጋሳና በሳባ መኩሪያ እንዲሁም ዲስኩር በደራሲ እንዳለጌታ ከበደና አማኑኤል መሐሪ ለታዳሚ እንደሚቀርብ ታውቋል።
“ህያው ብራና” መፅሐፍ የዓለም ሀገራት አይኖች ኢትዮጵያ ላይ እንደተተከለ የሚያሳይና የዚህም ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ ዕጅ የፃፈውን ታላቅና ህያው ብራና ለማግኘት ሌት ተቀን የሚኳትኑበትን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ነው ተብሏል።

Read 13458 times