Saturday, 20 February 2021 00:00

“ሀያል ፍቅር” መፅሐፍ ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   በጸሐፊና ተረርጓሚ ዮናስ ወልደ ፃዲቅ “ሀያል ፍቅር” የሚል ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ የተመለሰው የፍቅር የወንጀል መፅሐፍት የደራሲ ዳንኤላ ስቲል “No Greater Love” መፅሐፍ ነገ እሁድ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ አምስት ኪሎ በሚገኘው ራዲካል አካዳሚ አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በምርቃቱ ላይ የተለያዩ( ኪነ ጥበባዊ) መሰናዶዎች የሚቀርቡ ሲሆን ገጣሚያኑ ደምሰው መርሻ፣ ቅድስት እንዳለ፣ ኤፍሬም ስዩም፣ሰለሞን ሳህለ ትዕዛዙ፣ ምዕልቲ ኪሮስ፣ ፋሲል ምስጋናው፣ ዩሐንስ ሀብተማሪያም ቅድስት በላይ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡
ድህነትን፣ ገንዘብን፣ ፍቅርንና ስግብግበነትን የሚያሳየው መፅሐፉ፣ በ421 ገፆች ተቀንብቦ በ250 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ተርጓሚው ከዚህ ቀደም የእንግሊዘኛ ትርጉም (subtitile) እና “ሱፐር ጎል ስፖክን ኢንግሊሽ” የተሰኘ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሐፍ ማዘጋጀቱ የሚታወስ ነው፡፡


Read 12974 times