Monday, 22 February 2021 07:14

ማራኪ አንቀፅ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ሕግ 2
በጓደኞችህ ላይ እምነት አታሳድር፤ ጠላትህን እንዴት እንደምትጠቀመበት እወቅ!
ብያኔ
ጓደኞችህን ስጋ፤ ተጠንቀቅም፤ በፍጥነት ሊከዱህ ይችላሉና፤ በቀላሉ ለቅናት ስለሚጋለጡ፡፡ ሞልቃቃ፣ ባለጌና አምባገነነንም ይሆናሉና፡፡ የቀድሞ ጠላትህን ቅጠረው  ከጓደኝህ የበለጠ ታማኝ ይሆናል፤ ምክንያቱም ማረጋገጥ አለበትና፡፡ በእርግጥ ከጠላቶችህ ይበልጥ አጥብቀህ መፍራት ያለብህ ጓደኞችህን ነው፡፡ ጠላት ከሌለህም ጠላት የምታፈራበት ዘዴ ፈልግ፡፡
ሕጉ ሲተገበር
በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ሳልሳዊ ሚካኤል፣ የቤዛንታይንን በትረ መንግስት እንደሚጨብጥ ተገመተ። እናቱ ንግስት ቲኦደራ ገዳም ገብታ ቀለጠች፤ ፍቅረኛዋ ቲዎክቲስተስ ስለተገደለ፡፡ የዚህ ሴራ ዋነኛ መሪ ደግሞ ብሩህ ህሊና ያለው የሚካኤል አጎቴ ባርዓስ ነው፡፡ ወጣቱና ብዙ ልምድ የሌለው ሚካኤል ስልጣን  ሲይዝም በተንኮለኞች፤ በገዳዮችና ሴረኞች ባለስልጣናት ነበር የተከበበው። እናም በአቅራቢያው የሚያምነው ሰው ሲፈልግ ጓደኛው ባሲለስን አሰበ፡፡ ባሲለስ የመንግስት አስተዳደርና የፖለቲካ ዕውቀት የሌለው ነው፡፡ ከንጉስ ጋርም የተገናኙት ባሲለስ የንጉሳውያን የፈረስ መግሪያ ማዕከል ኃላፊም በነበረበት ወቅት ነው፡፡ የተዋወቁትም ከዓመታት በፊት ሚካኤል በፈረስ መግሪያው ሲለማመድ ፈረሱ ደንብሮ  ባሲለስ ሕይወቱን ባተረፈለት ድጋፍ እያደገ ሄደ፡፡ እጅግም ምርጥ ወደ ሚባል ትምህረት ቤት ሄዶ ተማረ፡፡ እናም ባሲለስ ከጥፍራም ገበሬነት ወደ ዘመናዊና የተማረ ባለስልጣንነት ተቀየረ፡፡ እናም ንጉስ ሳልሳዊ ሚካኤልን ከብልህ አጎቱ ባርዳስ ይልቅ እንደ ወንድም የሚቆጥረው ባሲለስን አማካሪ አደረገው፡፡
ባሲለስም ፈጣን ተማሪ ከመሆንም በላይ ንጉሱን በሁሉም ዘርፍ አማካሪ ሆነ። የባሲለስ ትልቁ ችግር ግን ገንዘብ የሌለው መሆኑ ነው፤ የባዛንታይንን ባለስልጣናት እንድልቅ ኑሮን ለመወዳደር፡፡ ችግሩን የተረዳለት ንጉስ ሚካኤል፤ የባሲለስን ደመወዝ በሶስት እጥፍ አሳደገው፤ ገንዘብንም ሰጠው፡፡ ከእቁባቶቹ አንዷንም ዳረለት። ይህ ሁሉ ሲደረግለት የሚካኤል አጎቱ ባርዳስ የጦሩ መሪ መሆኑ ታዲያ ለባሲለስ አልተመቸውም። እናም ባርዳስ ስልጣንህን ሊነጥቅ ይፈልጋል ሲልም በንጉሱና በአጎቱ መሀል ገባ፡፡ በንጉስ ሚካኤል ጆሮ ውስጥም መርዝ ጨመረ፡፡ ይህን ያደረገው አጎትህ ነው ሲልም  ባርዳስ እንዲገደል አደረገ፡፡
ንጉስ ሳልሳዊ ሚካኤልም ገንዘቡን አለገደብ ይረጭ ነበርና ችግር ላይ ወደቀ። እና ባሲለስ የተበደረውን ገንዘብ አንዲመልስለት ጠየቀው፡፡
ለንጉስ ሚካኤል በሚያስደነግጥ ሁኔታ ባቢለስ እንቢተኝነቱ ገለፀ፡፡ ንጉስም አስጊ ሁኔታ እንደተጋረጠበት ተረዳ፡፡ ምክንያቱም ደግሞ የቀድሞ ፈረስ ጋሪ ባሲለስ ከንጉስ በላይ ገንዘብ እንዳለው፣ በጦሩም  ውስጥና በሴኔት ውስጥ ብዙ ወዳጅ ማፍራቱን ማወቁ ነው፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በኋላም ንጉስ ሚካኤል ሳልሳዊ ከእንቅልፉ ሲነቃ፤ በመታደሮች መከበቡን አወቀ፡፡ ባቢለስም ወታደሮቹን ንጉሱን ደብድበው ሲገድሉት ቆሞ ተመለከተ፡፡ ንጉስ መሆኑን ካወጀ በኋላም የንጉስን ጭንቅላት በመያዝ  በቤዛንታይን በፈረስ ጋለበ፡፡
ትርጓሜ
ሳልሳዊ ሚካኤል እንደሚወደው ባሲለስም ይወደኛል ሲል የወደፊት ራዕዩን አጨለመ፡፡ ሲጀምር ባሲለስ ንጉስ በሚገባ አገለገለ፡፡ በምላሹም የንጉስን ሀብት፣ ትምህርትና ማዕረግ አገኘ በዚህም እየጠነከረ መጣ፡፡ ንጉሱም ከፍተኛ ስህተት መስራቱን ዘግይቶም ቢሆን ተረዳ፡፡ ግን የራሱን ሕይወት መጠበቅ የሚያስችለውን እርምጃ መወሰድ ይችል ነበር፡፡ ሆኖም፣ ጓደኝነትና ፍቅር የማንኛውንም ሰው ህሊና እንደሚጋርድ ነውና ንጉሱንም አሞኘው፡፡ ማንም ሰው ጓደኛዬ ይከዳኛል ብሎ ለማመን ይቸገራልና፣ ንጉስም አንገቱ እሰከሚቆረጥ ድረስ ይህን ማመን አልቻለም፡፡
ፈጣሪዬ አንተ ከጓደኞቼ ጠብቀኝ፣ ራሴን ከጠላቶቼ መጠበቅ እችላለሁና፡፡
(ቮልተር 1694-1778)
ኃይል ጠላት እንዲኖርህ ከፈለግህ፣ ጓደኛህን ምረጠው፤ መቼ ማጥቃት እንዳለበት ያውቅበታልና፡፡
(የፈረንሳይ ሚኒስቴር የነበረው ድያኔዴ ፓይትሬስ 1499-1566)
ሕጉ ሲተገበር
በቻይና የጥንቱ የሃን ስርወ መንግስትስ በደም አፋሳሽ መፈንቅለ  መንግስት ሥልጣን መያዝ የተለመደ ነበር፡፡ አንድ ጄኔራል ሥልጣን ከያዘ በኋላ አብረውት የነበሩት ጄኔራሎችና ልጆች ይገድላል፤ ሥልጣኑን እንዳይቀናቀኑት፡፡ ይሁንና ቆይቶም ቢሆን ሌላ ጄኔራል ተነስቶ ሥልጣን በመያዝ ንጉሱንና ልጆቹን ይገድላል፤ አብረውት የነበሩት ጓደኛ ጄኔራሎችንም እንዲሁ፡፡
በ959 ጄኔራል ቻኦ ኩአንይ ንጉስ ሱንግ ተብሎ ነገሠ፡፡ የመፈንቅለ መንግስቱን ታሪክ ጠንቅቆ የሚያውቀው ንጉስ ሱንግ፤ ሁኔታዎችን ካልቀየረ በአንድ ወይም በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚገደል ገመተ፡፡ እናም ይህ የመፈንቅለ መንግስት ሁኔታ መቀየር እንዳለበት ወሰነ፡፡ ለንግስቲቱም ክብር ግብር ጠራ፡፡ በግብሩም የጦሩ ታላላቅ አዛዦች ተጠርተው በሉም፤ጠጡም፡፡ በሰከሩም ጊዜ በጥበቃ የተሰማሩትን ወታደሮች አሰናበተ። ጄኔራሎቹም  እንገደላለን ብለው በፍርሃት ወደቁ፡፡ በተቃራኒው እሱም ከመንግስት ግልበጣ ሥጋት ነጻ ለመሆንና እነሱም በሰላም እንዲኖሩ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ንጉሱን ጠየቃቸው። ስልጣናቸውን ሁለቱም ተንደላቀው የሚኖሩበት የራሳቸው ርዕስት እንደሚሰጣቸው ቃል ገባ፡፡ ሁሉም ጀኔራሎች በነጋታው ሥልጣናቸውን ለቀቁ፤ ለንጉስም አደጋ የነበሩት ጄኔራሎች ወዳጅ ሆኑ፡፡ ከጄኔራሉ ሊዩ በቀር፡፡
“ሕግጋተ ሥልጣን ከተሰኘው የተርጓሚ ጌታሁን ንጋቱ መፅሐፍ የተቀነጨበ”

Read 2534 times