Saturday, 18 August 2012 11:33

ዳቢ ኮምፕሌክስ ህንፃ በጐርፍ ተጥለቀለቀ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሟል ተባለ

Written by  ሰላም ገረመው
Rate this item
(0 votes)

ቦሌ መንገድ ሳይ ኬክ ቤት ጐን ወደሚገኘው ዳቢ ኮምፕሌክስ ህንፃ በገባ ጐርፍ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት መውደሙን የህንፃው ባለቤት አቶ መንግስቱ ዳቢ ለአዲስ አድማስ ገለፁ፡፡ የቦሌ መንገድ ሲሠራ የውሃ ማውረጃው ቱቦዎች ስለተነሱ ምትክ እንዲሠራለት በተደጋጋሚ ጠይቀናል የሚሉት አቶ መንግስቱ፤ ሆኖም ቻይናዎቹ በመንገዶች ባለስልጣን ሲያላክኩ፤ መንገዶች ባለስልጣን በቻይናዎቹ ሲያላክኩ ተቀያሪ ነገር ሳይሠራ ቆይቷል ይላሉ፡፡ ሀሙስ ማታ በጣለው ሀይለኛ ዝናብ ከቲኬ ህንፃ፣ ከቴሌ መድሀኒአለም አቅጣጫ የሚመጣው ጐርፍ ቀጥታ ወደ ዳቤ ህንፃ የመኪና ማቆሚያ በመግባት ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉን አቶ መንግስቱ ይናገራሉ፡፡ በህንፃው ሊፍት እና በመኪና ላይ ጉዳት ከመድረሱም በተጨማሪ፤ የህንፃው ተከራዮች የሚጠቀሙበት መጋዘን ውስጥ ጐርፍ ገብቶ ጫማዎች፣ የተለያዩ አልባሳትና ንብረቶች መውደማቸውን ተናግረዋል አቶ መንግስቱ፡፡

በጐርፍ የገባውን ውሃ ለማስወገድ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ መሥሪያ ቤት መምጣቱን አቶ መንግስቱ ገልፀው፤ ነገር ግን ጋዜጠኞች ከመጡ አንሰራም፤ በግላችሁ ውሃውን አስመጥጡ በማለት ተመልሰው ሄደዋል ብለዋል፡፡

 

 

Read 3618 times Last modified on Saturday, 18 August 2012 11:36