Sunday, 28 February 2021 00:00

በእርግዝና ወቅት የልብ ምት በ20% ይጨምራል፡፡

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 እርግዝናንና የልብ ሕመምን የሚመለከት ሳይንሳዊ ጽሁፍ የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር February 18, 2020 አመታዊ ጉባኤውን ሲያካሂድ በJ. Igor Iruretagoyena MD Associate Professor Maternal Fetal Medicine University of Wisconsin አማካኝነት ቀርቦ ነበር፡፡ ይህን ሳይንሳዊ እውነታ ታነቡ ዘንድ የባለሙያ እገዛ በመጠየቅ ለንባብ ብለነዋል፡፡ ይህን ጽሁፍ በተለይም ለሙያዊ ስያ ሜዎች ፍቺውን የሰጡን እና
ሕመሙ ምን እንደ ሚመስል ያብራሩልን ዶ/ር ያየህይራድ አየለ ከቅዱስ ፓውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ናቸው፡፡ የልብ ህመም ሲባል በብዙ ምክንያቶች
ሊከሰቱ የሚችሉ በአይነታቸውም የተለያዩ ናቸው፡፡ በዚህ እትም እንድታነቡት የቀረበው በእንግሊዘኛው valvular heart disease ሚባለውን የ ልብ ህ መም አ ይነት ሲ ሆን ይ ህም በእርግዝና ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ተጽእኖ ነው፡፡ የሰው ልጅ ልብ ሲታይ አራት ክፍሎች ያሉት አካል ነው፡፡ እነሱም በላይኛው የግራ እና የቀኝ ክፍል የሚገኙት atria እና በታችኛው ግራ እና ቀኝ ክፍል ያሉት ventricles በመባል ይታወቃሉ፡፡ እርግዝና በተፈጥሮ ሰውነትን ወደከፍተኛ አካላዊ መጨናነቅ ውስጥ የሚከት ሲሆን ይህም የሚሆነው መሃጸን ውስጥ ለሚገኘው ጽንስ እድገት አመቺ የሆነ መኖሪያ ስፍራ ለመፍጠር ነው፡፡ በእርግዝና ወቅት ሰውነት በሚያካሂዳቸው ለውጦች በልብ እና በደም ዝውውር ላይ የሚከሰቱት አጋጣሚዎች የሚከተሉትን ይመስላሉ፡፡
• አንዲት ሴት በእርግዝና ወቅት በሰውነትዋ ያለው ደም ይዘት ከ30-50 % ሊጨምር ይችላል፤
• የልብ ምትዋ ደግሞ በ20% ይጨምራል፤
• የደም ግፊትዋ ደግሞ በ 5% ዝቅ ሊል ይችላል፤
እነዚህ ተፈጥሮእዊ ለውጦች ልብ ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራሉ፡፡ አንዲት ሴት ከማርገ ዝዋ በፊት ከግል ሃኪምዋ ጋር በመነጋገር የተለያዩ ቅድም ምርመራዎች ማድረግ ይገ ባታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ነባር የልብ ህመምተኛ ከሆነች በልብዋ ላይ የሚደርሰው ጫና የበረታ ይሆናል፡፡ ስለዚህም አንዲት በልብ ህመም የተጠቃች ሴት በእርግዝና ወቅት የልብ ህምሙ ሊያመጣባት የሚችለውን ጫና አስቀድሞ ለመገምገም የሚያስችሉ የተለያዩ ሞዴሎ ችን መጠቀም
የሚቻል ሲ ሆን በ ተለይም M odified W HO classification of maternal cardiovascular risk የተሰኘው አለምአቀፍ ሞዴል በሰፊው ተቀባይነት ያገኘ ሞዴል ነው፡፡ ይህ ሞዴል በ5 ክፍል የተከፈለ ሲሆን እናትየው ባለችበት ቡደን መሰረት ምን አይነት የልብ ምርመራ እና በምን ያክል ግዜ ልዩነት እንደምታደርግ ይጠቁማል፡፡ ሁሉም እርጉዝ እናቶች ከዚህ ቀደም የልብ ህመም ካለባቸው ወ ይም የ ልብ ህ መም እ ንዳለባቸው የሚጠረጠር ከሆነ በልብ እስፔሻሊስት እና በ Maternal Fatal Medicine Sub Specialist እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ በሌላ እስፔሻሊስት ሀኪም መታየት አለባቸው፡፡
Valvular heart Disease የሚከተሉትን የህመም ስሜቶችን ሊያሳይ የችላል፡፡
1. ትንፋሽ የማጠር ስሜት፤
2. ደረት የመውጋት ስሜት፤
3. ሰውነት የማበጥ፤
4. ደም መትፋት፤
5. እራስን መሳት፤
6. የመድከም ስሜት፤
7. ልብ ሲመታ መሰማት፤
8. የማያቁዋርጥ ሳል፤
አንዲት እርጉዝ ሴት እነዚህ ስሜቶች ከተሰሙአት በአፋጣኝ ሃኪምዋን ማየት አለባት። በሌላ በኩል Mitral Stenosis የሚባል የልብ ሕመም አለ፡፡ Mitral Stenosis የሚባለው የልብ በሽታ አይነት የMithral ቫልቭ ከመደበኛ መጠኑ ከ 4 – 6 Cm2 ሲያንስ ነው፡፡ ነገር ግን ሕመም መሰማት የሚጀምረው ከ2.5Cm2 ሲያንስ ጀምሮ ነው፡፡ ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው እንዲት ሴት በእርግዝና ወቅት ከተለመደው ግዜ በተለየ የደም ይዘትዋ 30 -50% ሲጨምር የቀድሞ የልብ በሽተኛ ስትሆን ግን በተጨማሪ በቀኝ ልብ መሃል የሚገኘው Mithral ቫልቭ ከመደበኛ መጠኑ ያነሰ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት ደም በልብ ውስጥ በበቂ ሁኔታ እንዳይዘዋወር ያግተዋል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ በቂ ደም ከልባችን እንዳይወጣ እና ወደሁዋላ ማለትም ወደሳንባችን እንዲመለስ
ያደርጋል፡፡ እነዚህም ክስተቶች ሰውነታችን ላይ የተላያዩ የህመም ስሜቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት ይሆናሉ፡፡
የልብ ሕመምን ለመከላከል ወይም ተጋላጭነትን ለመቀነስ አንዲት ለማርገዝ ያቀደች ወይም ያረገዘች የልብ በሽተኛ ሴት ማድረግ የሚጠበቁባትን ነገሮች መረጃዎች እንደሚከተለው ይጠቁማሉ፡፡
1. አልኮሆል መጠቀምን ማቆም፤
2. ሲጃራ ማጨስን ማቆም፤
3. አመጋገብን ማስተካከል ማለትም ጤናማ አመጋገብን መከተል፤
4. ጭንቀትን መቀነስ፤
5. በቂ እንቅልፍ ማግኘት፤
6. ከመጠን ያለፈ ክብደት ካለ ስለክብደት መቀነስ ከሃኪም ጋር መመካከር፤
7. ከሃኪም ጋር ያለውን የክትትል ቀጠሮ አክብሮ መገኘት…ማለትም ቀጠሮን አለማለፍ ወይንም አለመዝለል፤
8. በሃኪም የታዘዘ የአካል ብቃት እንቅማድረግ፤ ለተጠቀሰው የልብ ሕመም መጋለጥ ምክንያት ከሚሆኑት መካከል ሊስተካከሉ የሚችሉና ሊስተካከሉ የማይችሉ እውነታዎች አሉ፡፡
ሊስተካከሉ የማይችሉ፤
1. እድሜ ከ30 በላይ ከሆነ፤
2. መንታ እና ከመንታ በላይ ካረገዘች ፤
3. በበፊት እርግዝናዋ ግፊት እና ስክዋር ከገጠማት፤
4. በልብ ህመም የተጠቃች ከሆነች፤ የተጠቀሱት እውነታዎች የሚመለከቱዋት
እርጉዝ ሴት ሕክምናን በአግባቡ ከመከታተል ውጭ ታማሚዋ በራስዋ ልታሻሽለው የምትችለው ነገር የለም፡፡
ሊስተካከል የሚችል፤-
1. አልኮል እና ተመሳሳይ እጾችን መጠቀም፤
2. ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት፤
3. ያልተመጣጠነ ምግብ መመገብ፤
4. የደም ግፊት፤
5. የስክዋር ህመም፤
የተጠቀሱት ምክንያቶች ያሉባት ሴት ከህክምናው በተጨማሪ እራስዋም አኑዋኑዋሩዋን በማስተካከል ሕመምዋን ማሻሻል ወይንም መፍትሔ ማግኘት ትችላለች፡፡ እንዲት ሴት በሕክምና ባለሙያ ምክር መሰረት በእግባቡ በቂ ህክምና ካላገኝች እና ሕመምዋን ካልተከታተለች በእናትየውም ሆነ በጽንሱ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. በእናትየው ላይ ሊከሰቱ ክሚችሉት ችግሮች መካከል፡- ሳምባ ላይ ውሃ መቁዋጠር፤ የልብ ምት መዘበራረቅ ወ ይም የ ልብ መ ድከም፤ እንዲሁም
የእናትየው ህይወት ማለፍ ናቸው፡፡
2. በጽንሱ ላይ ደግሞ፡- ካለጊዜው መወለድ፤ አነስተኛ ክብደት እንዲሁም የጨቅላው ህጻን ህይወት ማለፍ ይገኙበታል፡፡


Read 9671 times