Monday, 01 March 2021 19:45

ሂላሪ ክሊንተን የመጀመሪያቸውን ልቦለድ መጽሐፍ ሊያሳትሙ ነው

Written by 
Rate this item
(2 votes)

የቀድሞዋ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ቀዳማዊት እመቤት ሂላሪ ክሊንተን “ስቴት ኦፍ ቴረር” የሚል ርዕስ የሰጡትን የመጀመሪያቸውን የልቦለድ መጽሐፍ በቅርቡ ለህትመት እንደሚያበቁ መነገሩን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ በመጪው ጥቅምት ወር መጀመሪያ በገበያ ላይ ይውላል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ መጽሐፍ ዋነኛ ትኩረቱን ያደረገው በሽብር ጥቃቶች ዙሪያ መሆኑን የጠቆመው ዘገባው፤ ሂላሪ መጽሐፉን ያዘጋጁት ሉዚ ፔኒ ከተባሉ አንዲት ታዋቂ ካናዳዊት የወንጀል መጽሐፍት ደራሲ ጋር በትብብር መሆኑንም አክሎ ገልጧል፡፡ በአሜሪካ ሴንት ማርቲንስ ፕሬስና ሲሞን ኤንድ ሹስተር በተባሉ ሁለት አሳታሚ ኩባንያዎች በእንግሊዝና በሌሎች የአለማችን አገራት ደግሞ በፓን ማክሚላን አሳታሚነት ለንባብ ይበቃል መባሉን ዘገባው ጠቁሟል፡፡ ሂላሪ ክሊንተን ከዚህ ቀደም በርካታ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸውን ያስታወሰው ዘገባው፣ ከእነዚህም መካከል በ2014
ለንባብ የበቃው “ሃርድ ቾይዝስ” እና በ2017 የታተመው “ዋት ሃፕንድ” እንደሚገኙበት ገልጧል፡፡


Read 8249 times