Sunday, 28 February 2021 00:00

“የአገዛዞች ቀይ መስመር” መፅሐፍ ዛሬ ገበያ ላይ ይውላል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 “የአገዛዞች ቀይ መስመር፤ ጭቆናን የመስበር ጽናቶች” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ አዲስ መፅሐፍ በዛሬው እለት ለአንባቢያን
ይበቃል። በተለያዩ የጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ በአዘጋጅነት፣ በዋና አዘጋጅነት እንዲሁም ጠንካራ ሂሳዊ ፅሑፎች በማህበራዊ ሚዲያዎች በመጻፍ የሚታወቀውና በዚህም ለተደጋጋሚ እስር የተዳረገው የጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ መፅሐፍ፤ የሃገሪቱን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና የህግ
ሂደቶች ይዳስሳል፡፡ በ220 ገጾች የተዘጋጀው “የአገዛዞች ቀይ መስመር”፤ በ180 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም መፃሃፍት ቤቶችና አዟሪዎች እጅ ይገኛል ተብሏል።

Read 8345 times