Saturday, 06 March 2021 13:07

የኮቪድ-19 ክትባት ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

        የኮቪድ 19 ክትባት ዛሬ ኢትዮጵያ እንደሚገባ  ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን ክትባቱን በብዛት በመውሰድ ኢትዮጵያ በ6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
የኢትዮጵያ መንግስት ጠይቆ የነበረውና በሚያዚያ ወር ይደርሳል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው 9 ሚሊዮን ክትባት ቢሆንም፣ የተገኘው 7 ሚሊዮን 620 ሺህ ያህሉ ብቻ መሆኑ ታውቋል።
መንግስት ለክትባቱና ተያያዥ ወጪዎች 13 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው አስታውቋል። ለድሃ ሃገራት እንዲከፋፈል 330 ሚሊዮን ክትባት የተዘጋጀ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለውን የምትወስደው ፓኪስታን መሆኗ ታውቋል።
በዚሁ መሰረት፤ ፓኪስታን 14 ሚሊዮን 640 ሺህ ክትባት ፤  ናይጄሪያ 13 ሚሊዮን 656 ሺህ፣ ኢንዶኔዥያ 11 ሚሊዮን 704 ሺህ 8 መቶ፣ ባንግላዴሽ 10 ሚሊዮን 908 ሺህ፣ ብራዚል 9 ሚሊዮን 22 ሺህ 4 መቶ፣ ኢትዮጵያ 7 ሚሊዮን 620 ሺህ ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ 5 ሚሊዮን 928 ሺህ ፣ ሜክሲኮ 5 ሚሊዮን 532 ሺህ እንዲሁም ግብፅ 4 ሚሊዮን 389 ሺህ ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል።


Read 701 times