Saturday, 06 March 2021 14:02

“ኢትዮጵያ ወደነበረችበት የዘመን ከፍታ” የኪነ-ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

      በ”ኢትዮጵያ” ሚዲያ ኮሙኒኬሽንና ኢቨንት ኦርጋናይዘር በየወሩ የሚካሄደው የኪነ-ጥበብ ምሽት የዚህ ወር መሰናዶ “ኢትዮጵያ ወደ ነበረችበት የዘመን ከፍታ” በሚል ይካሄዳል። ሰኞ የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም በአምባሳደር ሲኒማ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ ይካሄዳል። በዚህ የኪነ-ጥበብ ምሽት የመከላከያ ሃይላችንን ክብርና ሃላፊነት ከፍ የሚያደርጉ መሰናዶዎች የሚቀርቡ ሲሆን፣ ግጥም፣ ሙዚቃ መከላከያ ሃይሉን የሚወድሱ ንግግሮች፣ የስዕል ትዕይንቶችና መሰል ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶዎች እንደሚቀርቡ ታውቋል።

Read 10824 times