Saturday, 06 March 2021 14:14

ኔይማር በፑማ በዓመት 24 ሚ.ፓውንድ ያገኛል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

      በዓለም እግር ኳስ ከመጫወቻ ታኬታ ጋር በተያያዘ ትልቁን  የስፖንሰርሺፕ ውል ያስመዘገበው ተጨዋች ብራዚላዊው ኔይማር ነው፡፡
በፈረንሳዩ ክለብ ፓሪስ ሴንትዠርመን በመጫወት ላይ የሚገኘው ኔይማር ከአሜሪካው የትጥቅ አምራች ኩባንያ ናይኪ የነበረውን ውል በመተው ከፑማ ኩባንያ ጋር አዲስ ስምምነት ካደረገ በኋላ በዓመት 23 ሚሊዮን ዩሮ ክፍያ በማግኘት ከዓለም እግር ኳስ ተጨዋቾች በአንደኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡የእግር ኳስ ተጫዋቾች ከስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያዎች ጋር በየጊዜው በሚያደርጓቸው የውል ስምምነቶች ከፍተኛ ክፍያዎችን ያገኛሉ። አንዳንድ  ተጫዋቾች የረጅም ጊዜ ስምምነቶች በማድረግ ከፍተኛ ገቢ ሲያገኙ ሌሎች ደግሞ የነበሯቸውን ውሎች በማደስና አዲስ የትጥቅ ብራንድ በመምረጥ ገቢያቸውን ይጨምራሉ፡፡ ከዚህ በታች የቀረቡት በታኬታ የስፖንሰርሺፕ ውል  ከፍተኛ ክፍያ የሚያገኙ  አምስቱ ተጨዋቾች ናቸው፡፡

Read 860 times