Saturday, 13 March 2021 12:01

ለምርጫው ብልፅግና፣ ኢዜማ፣ እናት ፓርቲ… ከፍተኛ ቁጥር ያለው የእጩ ተወዳዳሪዎች አቅርበዋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

          125 የግል ተወዳዳሪ እጩዎች ተመዝግቧል
            47 የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው ይሳተፋሉ

               በዘንድሮ አገራዊ ምርጫ ብልፅግና ኢዜማ፣እናት ፓርቲ ከፍተኛውን የእጩ ቁጥር ያስመዘገቡ ሲሆን ኦነግና ኤፌኮ በምርጫው የማይሳተፉ ፓሪዎች ሆነዋል፡፡
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ለምርጫው በአጠቃላይ ለፓርላማና ለክልል ም/ቤቶች 2432 እጩዎችን ሲያቀርብ፣ ኢዜማ 1385 እንዲሁም እናት ፓርቲ 573 እጩዎች ያቀረቡ ሲሆን አብን 491፣ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ 472፣ህብር ኢትዮጵያ 253፣ባልደራስ 160፣ኢህአፓ 93፣ መድረክ 20 እጩዎች ማቅረባቸውን ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
በአጠቃላይ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚሳተፉበት በዚሁ ምርጫ 8209 እጩዎች ለፌደራል ፓርላማና ለክልል ም/ቤቶች ምርጫ በእጩነት መመዝገባቸውን ቦርዱ የገለፀው ቦርዱ፤ 125 የግል ተወዳዳሪዎች በእጩነት ተመዝግበዋል ብሏል።
በህጋዊነት ተመዝግበው ከሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ኦፌኮና ኦነግ አንድም እጩ ያላስመዘገቡ ፓርቲዎች መሆናቸውን የተገለፀ ሲሆን ሁለቱ ፓርቲዎች በራሳቸው ምክንያት ካልሆነ በቀር በቦርዱ ከምርጫው በቦርዱ እንዳልተገፉ ሰብሳቢዋ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል፡፡
ቦርዱ የፀጥታ ችግር አለባቸው በሚል በርካቶች በሰጉባቸው የኦሮሚያ ክልል፣ አራቱም የወለጋ ዞኖች በተሳካ ሁኔታ የእጩዎች ምዝገባ አከናውኖ ማጠናቀቁን አመልክቷል፡፡
በመጪው መጋቢት 22 ቀን 2013 በሚጀመረውና እስከ ሚያዚያ በሚቆየው የመራጮች ምዝገባ 50 ሚሊዮን መራጮች ይመዘገባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከ152 ሺህ በላይ መራጮችን የሚመዘገቡ ባለሙያዎች እንዲሁም ከ254 ሺህ በላይ ምርጫ አስፈጻሚዎች እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡

Read 12370 times